#የአሻራ ሚዲያ ጋዜጠኞች በመንግሥት መታሰር በሚመለከት: በውጭ አገር ከሚኖሩ የአሻራ ሚዲያ ቦርድ እና ድጋፍ ሰጭዎች ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ አሻራ ሚዲያ፣ እንደማንኛውም የሚዲያ ድርጅት፣ ዜ…

#የአሻራ ሚዲያ ጋዜጠኞች በመንግሥት መታሰር በሚመለከት: በውጭ አገር ከሚኖሩ የአሻራ ሚዲያ ቦርድ እና ድጋፍ ሰጭዎች ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ አሻራ ሚዲያ፣ እንደማንኛውም የሚዲያ ድርጅት፣ ዜና ሲያቀርብ፣ ዘጋቢ ፊልሞችንሲሰራ፣ የተለያዩ ባህላዊ፣ ወታደራዊና ሀይማኖታዊ ክብረ በአላትን ቦታው ድረስ እየተገኘ በቀጥታ ሲያስተላልፍ የቆዬ ድርጅት ነው። ባለፉት ጥቂት አመታት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለአደጋ የተጋለጡ የአማራ ማህበረሰብ አባላት የሚያስተላልፉትን የድረሱልኝ ጥሪ ሲያስተጋባ ቆይቷል፤ ከወለጋ፣ ከመተከል፣ እና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈናቀሉ ወገኖች የሚገኙበትን ሁኔታ ሲዘግብ፣ በህልውና ማስከበር ዘመቻው ወቅት ተጎድተው የተመለሱ ዘማቾችና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ሲዘግብ ቆይቷል። ባለፈው የህልውና ዘመቻ ተሳትፈው ህይወታቸውን ላጡ ዘማ…ቾች ቤተሰቦች: ያሉበትን ሁኔታ በመጠየቅ፣ አሻራ ሚዲያ ከቦርድ አባላቱ መዋጮ በመሰብሰብ እርዳታ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። አሻራ ሚዲያ፣ ሁከትና ብጥብጥ ባሉባቸው አካባቢዎች በመገኘት ሰላም እንዲመጣ ሲዘግብም ቆይቷል። የታጠቁ የአሻባሪ ኃይሎች ጉዳት በሚያደርሱባቸው አካባቢዎች ስልክ በመደወል ከተጠቂዎች ጋር በመነጋገር መረጃ ሲያደርስ የቆየ፣ አካባቢያቸውንና ራሳቸውን ለመከላከል የሚሰለጥኑ ፋኖዎች ሲመረቁ በቦታው እየተገኘ ሲያሰተላልፍ የቆየ የሚዲያ ድርጅት ነው። ይህን ሁሉ ሲሰራ የማንንም የፖለቲካ ፓርቲ ለመደገፍ ወይም ሌላውን ለመንቀፍ ሳይሆን፣ በየቀኑ የሚከሰቱ እውነታዎችን ለህዝብ ለማድረስ ካለበት የሚዲያ ተቋም ኃላፊነት አኳያ ነው። አሻራ የሚወግንለት ህዝብ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ የለውም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት: በአማራ ክልል በህግ ማስከበር ስም ሰላማዊ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ከመስርያ ቤታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው ማፈንና መሰወር የፌደራልና የአማራክልል መንግስታት የእለት ተእለት ተግባር ሆኗል። በዚህ አፈናም፣ ሦስት የአሻራ ሚዲያ ጋዜጠኞችና ሁለት የካሜራ ባለሞያዎች፣ በስራ ላይ እያሉ ከሚሰሩበት ስቱዲዮ ታፍነው ተወስደዋል። በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው ከአካባቢያቸው ወደራቀ ቦታ እንደተወሰዱ ማወቅ ተችሏል። የአሻራ ሚዲያ ጋዜጠኞች እሳከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ፍርድቤት ቀርበው ክስ እንዳልተመሰረተባቸውም ማወቅ ተችሏል። እኛ በውጭ አገር የምንኖር የአሻራ ሚዲያ የቦርድ አባላትና ደጋፊዎች የኢትዮጵያ መንግስት በ ‘አማራ ክልል’ በህግ ማስከበር ስም እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ማሸበር አሁኑኑ እንዲያቆምና በህገ ወጥ መንገድ ያፈናቸውን የአሻራንና ሌሎች ጋዜጠኞችን፣ እንዲሁም ሌሎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችና ማህበራዊ አንቂዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ በአፅንዖት እንጠይቃለን። በአፈና እና በእስር የሚመጣ ውድቀት እንጂ ፍትህ የለም። የህግ የበላይነት ምንጩ የህዝብ ድምፅን ማዳመጥ እንጂ ማፈን አይደለም። በመሆኑም መንግስት እየሄደበት ያለውን ደመነፍሳዊ ጉዞ መርምሮ ፣ ተገቢ የማስተካከያ እርምት እንዲወስድ በጥብቅ እናሳስባለን። በመሳሪያ፣ በአፈና፣ በማሰር የሚፀና መንግስት እንደሌለም እናምናለን። የሀገራችን መፍትሄ አካታች ውይይት እና ንግግር፣ የፖለቲካ ማሻሻያ፣ የአስተዳድር እና የአሰራር ማስተካከያዎች እንጂ እስር አይደለም። ለመላው የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮች አሻራ በቅርብ ቀን የነበሩበትን ስህተቶች አርሞ፣ የበለጠ ተደራሽ እና ተመራጭ የሚዲያ ተቋም ሆኖ ስራውን የሚያስቀጥል መሆኑን ስንገልፅላችሁ ታላቅ ወገናዊ እና ሙያዊ ክብር ይሰማናል። “አሻራ የአይበገሬዎች ልሳን” ዋሽግተን ዲሲ፣ አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply