የአሻራ ምልከታ-የተፈናቃዮች ሁኔታ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013ዓ.ም)  ማዳን ባይችሉ ቀብራችንን እንኳ በወግ ሳያረጉት ቀርተዋል፡፡…  የተረፍነውንም በርሃብ ለመጨረስ መንግስት በሩን ዘግ…

የአሻራ ምልከታ-የተፈናቃዮች ሁኔታ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013ዓ.ም) ማዳን ባይችሉ ቀብራችንን እንኳ በወግ ሳያረጉት ቀርተዋል፡፡… የተረፍነውንም በርሃብ ለመጨረስ መንግስት በሩን ዘግ…

የአሻራ ምልከታ-የተፈናቃዮች ሁኔታ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013ዓ.ም) ማዳን ባይችሉ ቀብራችንን እንኳ በወግ ሳያረጉት ቀርተዋል፡፡… የተረፍነውንም በርሃብ ለመጨረስ መንግስት በሩን ዘግቷል፡፡ የቆሰሉትም ህክምና እጦት ላይ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ አሁን ላይ የተጣራ መረጃ አሻራ ባያገኝም በመተከል እና አካባቢው የተፈናቀለው የህዝብ ቁጥር ከ100 ሺ እስከ 150ሺ ይገመታል፡፡ 60ሺ አካባቢው በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ሲገኙ፣ ቡለን ወረዳ የሚገኘው የተፈናቃይ ቁጥር ደግሞ 50 ሺ ደርሷል፡፡ በመተከል በቀን 14 የሞቱት ሰዎች ቁጥር 280 አካባቢ እንደደረሰ አሻራ ሰምቷል፡፡ 17 ሰዎች ጉባ አይሲድ ከተባለ በቀን 15 ሲታረዱ፣ 6 ተቃጥለዋል፡፡ ድባጤ ደግሞ በቀን 16 አስራ ስምንት ሰዎች ተገለው ተገኝተዋል፡፡ ቡለን ወረዳ በቀን 16 በአንድ ጊዜ 207 ሰዎች በተሽከርካሪ ተቆፍሮ በጅምላ ተቀብረዋል፡፡ የመተከል ገጠሩ አካባቢ በሰው አስከሬን ጠረኑ ተቀይሯል፡፡ ገዳይ ቡድኑም ከሱዳን እና ከሀገር ውስጥ ካሉ መንግስታዊ ሀይሎች ጋር ሆኖ የበለጠ እየተዘጋጀ ሲሆን፣ አብዛኛውን የታጣቂው ደጋፊ አመራር ዱር ቤቴ ብሎ ጫካ ገብቷል፡፡ የመንግስት መዋቅሩ ሙሉ በሙሉ ዝግ የሆነ ሲሆን፣የባንክ አገልግሎት እንኳን ከቆመ ሳምንት አልፎታል፡፡ ማዕከላዊ መንግስቱ ይሄ ነው የተባለ ሀይል አልላከም፡፡ እርዳታም አላደረሰም፡፡ የአስከሬን መሸፈኛ ዳውጃ እንኳን ማቅረብ ስላልቻለ ንፅሃንን ተደራርበው እንዲቀበሩ ሆኗል፡፡ በዚህ ላይ የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ሀይማኖቱ በሚፈቅደው መንገድ ይቀበሩ አለማለታቸው ትዝብት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ የቆሰሉት የሚታሸጉበት ሻሽ እንኳን ማግኘት ያልቻሉ ሲሆን፣ የሚበላ ነገርም እስካሁን ማቅረብ አልተቻለም፡፡ ከዚህ ቀደም በገቢዎች ሚኒስትር በኩል እርዳታ የተደረገ ምግብ እና አልባሳት በአመራሮች ተዘርፎ ለተፈናቃዮች ሳይደርስ ቀርቷል፡፡ አሁንም የመንግስት መዋቅሩ ስለተበላሸ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ በስርቆት ሰበብ ለታጣቂው እየቀረቡ ሲሆን ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስራ አስኪያጁ ተገድሎ ገንዘቡ መዘረፉ አሻራ ያስታውሳል፡፡ በመንግስት መዋቅሩ ድክመት ምክንያት ኢ-መደበኛ ታጣቂው ፊት ለፊት ቀስት ይዞ ከኃላው የያዘው የቡድን መሳሪያ ከመንግስት ሀይል የበለጠ ነው፡፡ ልክ ህወኃት ሚሳዔል ታጥቆ እንደነበረው ሁሉ የመተከል ታጣቂዎችም ሆነ ኦነግ ከበባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ ሲሆን ፣አማራው ደግሞ እንኳን መሳሪያ ዘንግ እንዳይዝ መንግስታዊ ጫና ይደርስበታል፡፡ ከዚህ በፊት ታጥቆ ራሱን ህዝቡ ይከላከል ቢባልም ወደ መሬት አልወረደም፡፡ የታጠቁትም ከአማራ ውጭ ያሉት ናቸው፡፡ የአማራ ክልል አመራር በአብዛኛው አዳሪ እና የስልጣን ጡረተኛ በመሆኑ በጃዊ እና በጓንጓ ወረዳዎች ጥቃት ሲደርስ በዝምታ ተመክቷል፡፡ አብዛኛውን አውርቶ አዳሪ ፣ህዝቡም በካድሬዎች ወሬ ጠግቦ አዳሪ መሆኑ ዜጎች ሲጨፈጨፉ ዋስትና አሳጥቷቸዋል፡፡ በአማራ ክልል ድንበር የአማራ ልዮ ሀይል እንዳይገባ መከላከያ እየጠበቀ ሲሆን፣መከላከያ ንፅሃንን ግን ለመጠበቅ አልተቻለውም ፡፡ ይህ ደግሞ የፖለቲካው መበስበስ ውጤት መሆኑ ይሰመርበት፡፡ ባለፈው በመተከል በተደረገው ስብሰባ ፋና፣ኦሮሚያ ቴሌቪዝን(OBN) እና ኢቴቪ ሲገኙ የጉዳዮ ባለቤት አማራ ቴቪ ግን አልተገኘም ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የህዝቡ ስሜት እንዳይሰማ ነበር፡፡ በአብይ አህመድ ምርጫ የሄዱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የገዳዮችን ድምፅ በማስተጋባት የተገዳዮችን ሞት አራክሰዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የአማራ ክልል አመራሮች ቆራጥ ውሳኔ ሲወስኑ አይታይም፡፡ በጎጥ የተጨማለቁ እና በድንቁርና የማቀቀ፣የፖለቲካ ደዌ ያለባቸው በመሆኑ ከአንደበት ያለፈ ተግባር ነጥፎባቸዋል፡፡ ህዝቡም በአንደበታቸው እየተደለለ ዝምታ ላይ ተኝቷል፡፡ በሌላ ክልል የሚኖረው አማራ ግን ሰው ሆኖ የመኖር መብቱ ተገፎ ሲታመም መታከም፣ ሲራብ መብላት እንኳን አልችል እንዳለ የመተከል ተፈናቃዮች ጋር በስልክ ባደረግነው ቆይታ ተረድተናል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply