#የአሻራ ዕይታዎች #በአማራ ክልል ህግ ማስከበር የሚለው አካሄድ አገርን የሚያፈርስ ህዝብን የሚያጨራርስ የመሰሪዎች ስውር አጀንዳ መሆኑ ተገለፀ ! ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ከትህነግ/ህወሃት ጫካ የተቀዳው አማራን በጠላትነት ፣ ጨቋኝነት የሚፈርጀው ህገመንግስት ማህበረሰባችን /አማራውን ለይቶ ለመምራት የተዘጋጀ በመሆኑ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣት ወደ ለየለት ጀኖሳይድ ተቀይሯል። ለውጥ መጣ ከተባለ ጀምሮ በተለይም የህወኃት/ኢህአዴግ የጡት ልጅ የሆነው ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና ስርዓት ከግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ አማራ ክልልን የጦስ ዶሮ ለማድረግ ህግ ማስከበር በሚል ሽፋን የተደረገው መንግስታዊ ሽብር አማራን የማዳከም አንዱ አጀንዳን መሆኑን አሻራ አረጋግጣለች ። ስርዓት ለአንድ ሃገር እና ህዝብ የግድ አስፈሊጊ መሆኑንም እናምናለን።ነገር ግን ለአማራው ማህበረሰብ ተለይተው የሚሰጡ ውንጄላዎች፣የታቀዱ ኦፕሬሺኖች እና የተጠና ወታደራዊ ድርጊት አማራን አንገት የማስደፋት እና ቀጥቅጦ የመግዛት አገዛዝ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ነው። አደራን የማይሸክም እና ትውልድን የሚበላ ስርዓት ስታዋቅር እንዲህ ሞትህን በአደባባይ ሊያወጡት ሁሉ አይፈልጉም። በተደጋጋሚ እንደምንለው #የአማራው ችግር ዕራሱ አማራው ነው የምንልህም ቢያንስ የህዝብን ግብር እየተቀበለ የጠ/ሚ ውን ውሎ ሲዘግብ የሚውል ሚዲያ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በአንድ ጀምበር ሲጨፈጨፉ ግን መዘገብ አልቻሉም ነበር። ስለሆነም በተለይም ለብአዴን አመራሮች ድሮ ለህወኃት ስትላላኩ እንደነበር አረጋግጣችሁልናል። አሁን ደግሞ ለኦህዴድ ማጎብደዱን ቀጥላችሁበታል። ህዝባችን ማደናገሩን ትታችሁ የተወለዳችሁበትን ማህበረሰብ አገልግሉ፣ ወይ አቋማችሁን አሳውቃችሁ ህዝቡን ለባርነት መሸጣችሁን ግልፅ አድርጉለት። መንግስታዊ ጠባቂነትን ተውት። መዳኛ መንገዱ ልክ እንደ ወደረኞቻችን ስንደራጅ እና የፓለቲካ የበላይነት ካመጣን ብቻ ነው ። ሲጠቃለል በሰሞንኛው የብአዴን ስብሰባ ምንም የተለያየ ነገር አልተሰማም። የተለመደውን የጠላቶቻችን አካሄድ አጀንዳ ተቀባይ በመሆን ህዝባቸውን በመክዳት ኦህዴድ መራሹ ፌደራል ስርዓትን አካሄድ በመድገም ሌላ ጥፋት ለማዋለድ ስብሰባው መጠናቀቁን የውስጥ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላቶችህ የአብራክህ ክፋዮች፣ተልከስካሾች፣ቅርብ አደሪዎች፣መስሎ ኗሪዎች የሆኑት የአማራ ህዝብ አመራር ተብየዎች ናቸው። ከእነርሱ የምጠብቀው ነገር እንደሌለ መላው የአማራ ክልል ህዝብም በአንክሮ የተረዳ ስለሆነ ራስህን/ራሽን ለትግሉ አሳልፈህ ስጥ/ሰጪ። እየተካሄደ ያለው ዘር ማጥፋት ነው።በፓለቲካ መዋቅሩ የሚደረስብን ጥቃት መመከት የምትችለው ስርዓቱንና ስሪቱን በመታገል ነው። የአማራ አመራሮች ለሆዳቸው ያደሩ ግብዞች ስለሆኑ የአማራ ህዝብ መዳኛ መንገዱን አሁን መወሰን እንዳለበት ብዙዎች በአደባባይ ሃሳባቸውን እየገለፁ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post