የአቡነ ዘርዐ-ብሩክ ሃይማኖታዊ ንግሥናና በድምቀት የሚከበረውን የግዮን አመታዊ ክብረ-በዓል መሳተፍ የሁሉም ድረሻ ሊሆን ይገባል! ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአቡነ ዘርዐ-ብሩ…

የአቡነ ዘርዐ-ብሩክ ሃይማኖታዊ ንግሥናና በድምቀት የሚከበረውን የግዮን አመታዊ ክብረ-በዓል መሳተፍ የሁሉም ድረሻ ሊሆን ይገባል! ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአቡነ ዘርዐ-ብሩክ ሃይማኖታዊ ንግሥናና ለ5ኛ ጊዜ በድምቀት የሚከበረውን የግዮን አመታዊ ክብረ-በዓል ከምንጊዜውም በላይ በድምቀት ለማክበር በወረዳው ኮሚቴ ተዋቅሮ እቅድ ታቅዶ ወደ ስራ በመግባት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በበዓሉ በርካታ ታዳሚዎች እንዲሳተፉና የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር ለማድረግ የህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ በዓሉን ሳቢና ማራኪ ለማድረግ ተግባርና ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ኮሚቴዎች አካባቢን በማፅዳት፣ ሀብት አፈላላጊ በመሆን፣ የወረዳውን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ሃብት በማስተዋወቅ፣ የአካባቢውን ፀጥታ የሚያስከብር ግብረ ሀይልና የመስተንግዶ ኮሚቴ በማዋቀር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የወረዳዋን እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶችንና ወረዳዋን ሊያስተዋውቁ የሚችሉ ባህላዊ ምግብ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች በማዘጋጀት እንግዳ አክባሪነታቸውንና ተቀባይነታቸውን በተግባር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ የወረዳዋ የቱሪስት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመር በመሆኑ ትራንስፖርት ችግር እንዳይገጥም ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በጋራ በመሆን ከወዲሁ የቅድመ-ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ነዉ፡፡ አንዳንድ ሰርጎ ገቦች የፀጥታ ችግር እንዳይፈጥሩ፣ ብጥብጥና ግጭት እንዳይከሰት በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የፀጥታ ሃይሉ ስምሪት ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዓሉን በተለየ ሁኔታ ለማክበር የአካባቢው ተወላጆች፣የሃገር ውስጥና የውጭ ጎብኝዎች የበዓሉ ተሳታፊ ሲሆኑ የአካባቢውን ማህበረሰብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ስለሚያደርግ በወረዳዋ የሚመረቱ እንደ ቅቤ፣ ማርና ሌሎች ምርቶችን እንዲሁም የእደ-ጥበብ ውጤቶችን በበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በተዘጋጁ የገበያ ቦታዎች ላይ በማቅረብ የአካባቢውን ምርት ከማስተዋወቅ በላፈ የተሻለ የግብይት ስዓት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ መረጃው ከሰከላ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply