የአቢሲንያ ባንክ አሚን አዋርድ ሁለተኛ ዙር የሥራ ፈጠራ ውድድር” የመዝጊያ መርሐ ግብር እሁድ ሰኔ 9 ቀን 2016ዓ.ም ይካሄዳል ተባለ፡፡

አሚን አዋርድ የተሰኘው የሥራ ፈጠራ ውድድር” ከወለድ ነፃ በሆነው የአቢሲኒያ አገልግሎት በኩል መዘጋጀቱን ያስታወቀው ባንኩ የስራ ሀሳብ ይዘው የመነሻ ገንዘብ ያጡ ወጣቶችን በማወዳደር ከ200 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የሚሸልም የውድድር መርሃግብር ነው።

የአቢሲኒያ ከወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት ቢዚነስ ሰርቪሲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበጋዝ ይማም ፤“የአሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር” ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ የውድድር ሐሳቦችን በከፍተኛ ፉክከር በተለያዩ ጊዜ ሲያወዳድር መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

አቶ አበጋዝ በዚህ በሁለተኛ ዙር የአሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር ላይ 1 መቶ 80 ተወዳዳሪዎች ሃሳባቸውን አቅርበዋል ነው ያሉት።

ተወዳዳሪዎች ከመላው የአገራችን ከልሎች የመጡና በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና የሥራ ተሞከሮ ባላቸው ዳኞች ሲዳኙ መቆየታቸውንም ነግረውናል።

በውድድሩ ላይ የተለያዩ ምዕራፎችን በብቃት በማለፍ በብዙ መለኪያዎች ነጥረው የወጡ ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃን በማግኘት አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ባንኩ ከብር 200 ሺህ እስከ ብር 1ሚሊዮን ብር እንደሚያበረክ የገለፁት ደግሞ የፋይናሲንግ ቢዚነስ ዳይሬክተሩ አቶ ነቢል መሃመድ ናቸው ።

በልዑል ወልዴ

ሰኔ 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply