የአባ ገዳዎች ማብራሪያ

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በገዳ ስርዓት መሠረት ዕውቅና እና የላቀ ደረጃ ሰያሜ መስጠቱን የኦሮሞ አባገዳዎች ሕብረት አስታወቀ።

የቱላማ አባ ገዳና የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ፀኃፊ ጎበና ሆላ እሬሶ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕዉቅና የተሰጠው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማስቀጠል ባደረጉት ተጋድሎ  ነው።

በገዳ ስርአት ውስጥ አባ ገዳዎች በባህላዊ መንገድና የተለያዩ ጉዳዮችን መሰረት አድረገው የስም ስያሜና ዕውቅና መስጠት እንደሚችሉ የገለጹት ደግሞ የኦሮሞ ታሪክ እና ባህል አጥኝው አለማየሁ ሀይለ ናቸው።

የኦሮሞ አባገዳዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ስያሜ “አባ ቢያ, አባ መላ, አባ ጉራቻ” የሚል ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply