You are currently viewing የአብኑ ተወካይ አቶ አበባው ደሳለው ሊያቀርቧቸው የነበሩና ሳይፈቀዱ የቀሩ ጥያቄዎች አመሰግናለሁ የተከበሩ አፈ ጉባኤ! አመሰግናለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር! ጥያቄዎቼን እንደሚከተለው አቀርባለ…

የአብኑ ተወካይ አቶ አበባው ደሳለው ሊያቀርቧቸው የነበሩና ሳይፈቀዱ የቀሩ ጥያቄዎች አመሰግናለሁ የተከበሩ አፈ ጉባኤ! አመሰግናለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር! ጥያቄዎቼን እንደሚከተለው አቀርባለ…

የአብኑ ተወካይ አቶ አበባው ደሳለው ሊያቀርቧቸው የነበሩና ሳይፈቀዱ የቀሩ ጥያቄዎች አመሰግናለሁ የተከበሩ አፈ ጉባኤ! አመሰግናለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር! ጥያቄዎቼን እንደሚከተለው አቀርባለሁ። 1) ባለፉት 30 አመታት በተለይም ባለፉት 4 ዓመታት በተለያዩ ብሄሮች ላይ በጣም በተደጋገሚ ሁኔታ ደግሞ በአማራ ንጹሃን ላይ የሚደርሰው ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ፣ ጅምላ ፍጅት፣ የሀብት እና ንብረት ውድመት፣ የሰላማዊ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል ምንጩ ትህነግ ያነበረውና የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት ሳያካትት የተቀረፀው የኢፌደሪ ህገ መንግስት እና እሱን ተንተርሰው የተዘጋጁ የክልል ህገ መንግስቶች እንደሆነ በዘርፉ ሙሁራንና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይጠቀሳል። ምክንያቱም የብዙ ክልሎች ህገ–መንግስት አንድን ክልል ለአንድ ነባር ህዝብ ብሎ ለሚጠራው ብሄር የሚሰጥና ሌሎችን ብሄሮች ደግሞ መጤና ሰፋሪ ብሎ የሚከፋፍል ነው። የኢፌዴሪ ህገ–መንግስትና የክልሎችም እንዲሻሻል ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ተጠይቆ እስከአሁን አዎንታዊ መልስ አልተገኘም። አገራችን እያጋጠማት ላለው መዋቅራዊና ህግ ሰራሽ ችግሮች ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ያሳተፈ ህገመንግስት ማሻሻያ ማድረግ ዘላቂ መፍትሄ ነው ብሎ መንግስትዎ ያምናል ወይ? ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ የደረሰውን ማንነት ተኮር የአማራ ብሔር ተወላጆችን ጭፍጨፋ ጨምሮ ከዚህ በፊትም የተፈፀሙ ማንነት ተኮር ፍጅቶች የየአካባቢው የመንግስት አመራሮች አንዳንዴ በቀጥታ፣ ሌላ ጊዜ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉበት እንደሆነ ከጥቃት የተረፉ ሰዎች ይገልፃሉ። ጥቃቶች ሲፈፀሙም አስቸኳይ ርምጃ በመውሰድ ጉዳት የመቀነስ ስራ አይሰራም፣ በቶሎ ሲያስቆሙ አይታይም። እንዲያውም ጭፍጨፋው ከመከሰቱ በፊት ከነዋሪዎች መሳሪያ በመግፈፍና አፋጣኝ እርምጃ ባለመውሰድ እንዲሁም ሲጠየቁም ከበላይ ታዝዤ ነው እያሉ የእልቂቱ ተባባሪ ሲሆኑ ይታያሉ። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስልጣን እርከን ውስጥ የነበሩ ጀነራል ኦዲፒ በደብዳቤ ትዕዛዝ ጭምር ሸኔን እንዲደገፍ ትእዛዝ ይሰጥ ነበር ሲሉ ለኤልቲቪ ቴሌቪዥን ተናግረው ነበር። ከዚህ በፊትም ከ20 በላይ ባንኮች የተዘረፉት መንግስት ጨፍጫፊ ቡድኑን ለማጠናከር ነው ተብሎ ይነሳል። እነዚህንና የመሳሰሉ ምክንያቶችን በመዘርዘር ብዙ ሚዲያዎች ከዚህ ዘግናኝ እልቂት ጀርባ የመንግስት መዋቅርና ባለስልጣናቱ አሉበት ይባላል። ለዚህ ክስ ምላሽዎ ምንድነው? በተጨማሪም በአሁኑ ሰአት ኦነግ ሸኔ፣ የቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ግምባር፣ የጋምቤላ ነጻ አውጭ ግምባርና ሌሎች የአሸባሪ ሃይሎች በሙሉ ከመንግስት የጸጽታ ሃይሎች ጋር የሚከተሉት መደበኛ (ኮንቬንሽናል) ጦርነት ሳይሆን የሽምቅ ውጊያ እንደሆነ ይገለፃል። ለዚህ መፍትሄ ደግሞ ጠንካራ የፀረ ሽምቅ ሀይል ማዘጋጀትና ማሰማራት፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ማደራጀት፣ ማስታጠቅና ማሰልጠን ይገባ ነበር። ይህን መስራት ያልተቻለው ለምንድን ነው? በተጨማሪም በአዲስ አበባና በአማራ ክልል የአገር ባለውለታ ፋኖዎችና አንቂዎችን ያለፍርድቤት ትእዛዝ ህገወጥ እስር ቀጥሏል። መንግስት እነዚህን ዜጎች በቅርበት አወያይቶ የሰላም አጋር ለማረግ ምን ያህል ሰርቷል? ይህ የአፈና ድርጊት የሰላም እጦቱን አያባብሰውም ወይ? አመሰግናለሁ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply