You are currently viewing # የአብን ስራ አስፈፃሚና የህ/ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ የሚከተለውን ከትበዋል!! ክርስቲያን ታደለ ሹመኛ ነው? ***** ስንት አገራዊና የሕዝብ አንገብጋቢ ጉዳዮች ባሉበ…

# የአብን ስራ አስፈፃሚና የህ/ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ የሚከተለውን ከትበዋል!! ክርስቲያን ታደለ ሹመኛ ነው? ***** ስንት አገራዊና የሕዝብ አንገብጋቢ ጉዳዮች ባሉበ…

# የአብን ስራ አስፈፃሚና የህ/ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ የሚከተለውን ከትበዋል!! ክርስቲያን ታደለ ሹመኛ ነው? ***** ስንት አገራዊና የሕዝብ አንገብጋቢ ጉዳዮች ባሉበት በዚህ ወቅት ስለግላዊ ነገሮች ማውራት ተገቢ እንዳልሆነ አምናለሁ። ይህን የፃፍኩትም እውነታው እንዲታወቅና ታሪክና ትውልድ የየራሳቸውን ብይን መዝግበው እንዲያልፉ ነው። ኢትዮጵያ ያካሄደቺውን 6ኛ ዙር አገርአቀፍ ምርጫ ተከትሎ ባለው የክልል/ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል መንግስት ምስረታ ላይ ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በአስፈፃሚነት የማካተት አዲስ ባሕል ጀምሯል። በዚህም የአብን 3 አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን አመራሮች በፌዴራልና ክልል/ከተማ አስተዳደር ልዩ ልዩ ቦታዎች ላይ ሹመቶችን ሰጥቷል። ሹመቶችም በየደረጃው ባሉ የእንደራሴ ምክር ቤቶች ፀድቀዋል። በሌላ በኩል አብን በ6ኛው ዙር አገርአቀፍ ምርጫ በነበረው ተሳትፎ 5 የፌዴራል ፓርላማ ወንበሮችንና 13 ደግሞ የአማራ ክልል ምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፏል። በዚህም አብን በተለይ በፌዴራል ፓርላማ መቀመጫ ከገዥው ፓርቲ በመቀጠል ወንበር ያገኘ በመሆኑ በምክር ቤቱ አሰራርና ደንብ መሰረት በምክር ቤቱ ወንበር ካገኙት ኢዜማ፣ የጌዴዖ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የቁጫ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በተለዬ ልዩ መብቶች አሉት። ከልዩ መብቶቹ መካከልም አብን የተፎካካሪ ፓርቲዎች መሪ (Minority Leader) ሆኖ ለዚህ የሚሰየመው የአብን የምክር ቤት አባልም የፓርላማው የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ትይዩ ሆኖ በምክር ቤተረ አባላት መብቶችና ጥቅማጥቅሞች መመሪያ ላይ በዝርዝር የተገለፁ ጥቅማ ጥቅሞችና መብቶችን ያገኛል። ለአብነት ለመጥቀስ ያህል መኪናና ነዳጅ፣ ቢሮና የቢሮ ሰራተኞች፣ ወዘተርፈ ተዘርዝረዋል። (ለዝርዝር መረጃው ውሳኔ ቁጥር 43/2012 መመሪያ ላይ አንቀጽ 8 ይመልከቱ።) በተመሳሳይ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤቱን አሰራር፣ አደረጃጀትና ሚና በሚደነግገው ደንብ ቁጥር 6/2008 እንዲሁም በውሳኔ ቁጥር 2/2014 እና 3/2014 መሰረት የምክር ቤቱን ሥራዎች የሚመሩ የአማካሪ ኮሚቴና የአስተባባሪ ኮሚቴ የሚባሉ እንደቅደምተከተላቸው የፓርላማውን አስተዳደራዊና የፕሮግራም ዘርፎች የሚመሩ ኮሚቴዎች አሉ። ሁለቱም ኮሚቴዎች ላይ የገዥው ፓርቲና የተፎካካሪ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት አሉባቸው። በሁለቱም ኮሚቴዎች ላይ አብን ተወክሏል። የምክር ቤቱ አማካሪ ኮሚቴና አባላቱም በውሳኔ ቁጥር 2/2014 የተወሰነ ነው። በዚህ ኮሚቴ የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ተካተዋል። ከኢዜማ አንድ ሰው የአማካሪ ኮሚቴ አባል ሆነው ተካተዋል። በውሳኔ ቁጥር 3/2014 ደግሞ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ተግባርና ኃላፊነት የተወሰነ ሲሆን በውሳኔ ቁጥር 4/2014 ደግሞ የቋሚ ኮሚቴዎቹ ሰብሳቢዎች፣ ምክትል ሰብሳቢዎችና አባላት ተወስኗል። ከእነዚህ ቋሚ ኮሚቴዎች መካከል የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴን በሰብሳቢነት እንድመራ እኔ ክርስቲያን ታደለ ተካትቻለሁ። ከኢዜማ አንድ ሰው እና ከጌዴዖ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አንድ ሌላ ሰው ደግሞ በምክትል ሰብሳቢነት ተካተዋል። ዘግይቶም ቢሆን የአብን የምክር አባላትን ጨምሮ የሌሎችም የተፎካካሪ ፓርቲዎች በየቋሚ ኮሚቴዎቹ በአባልነት እንዲካተቱ ተደርገዋል። አብን ለምን የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት መብት ተሰጠው? ዓለምአቀፋዊ የፓርላማዎች አሰራር መርኅ እንደሚያሳየው የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ (Public Accounts Committee-PAC) የሚመራው በተፎካካሪ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ነው። የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ ብቻቸውን የተፎካካሪ ድምጽ ሆነው ፓርላማ በነበሩበት ዘመን፤ ቋሚ ኮሚቴው በተፎካካሪ ይመራል በሚለው መርኅ መሰረት፤ አሁን አብን በሰብሳቢነት የሚመራውን ቋሚ ኮሚቴ ሲመሩት ነበር። በሌላ ጊዜ ደግሞ አጋር ፓርቲ ይባሉ ከነበሩ የተወከሉ የምክር ቤት አባላት መርተውታል። በየመሀሉ በስተቀሮች አልነበሩም ማለት ግን አይቻልም። ዋና አመክንዮውም መንግስት ራሱ ያወጣውን ወጪ ራሱ ተቆጣጣሪ መሆን ስለማይችል የኦዲት ቅቡልነትን በማስፈን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ነው። ለCheck and Balanceም የተሻለ በመሆኑ ነው። የአብን የፓርላማ አባል ክርስቲያን ታደለ ብቻ ነወይ? በመጀመሪያ በምክር ቤት ውስጥ ያሉ የእንደራሴነት ኃላፊነቶች በሙሉ የምክር ቤት አባል አባል የሆኑ ብቻ የሚያገኟቸው ልዩ መብቶች ናቸው። በዚህ የተነሳም «ሥልጣን መጋራት» በሚል ማዕቀፍ ውስጥ የሚካተቱ አይደሉም። በሁለተኛ ደረጃ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴን ለመምራት ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች የበለጠ ወንበር ስላለው ልዩ መብት አለው። አብን በፓርላማው 5 ተመራጮች እያሉት ለምን ክርስቲያን ታደለ ሰብሳቢ ሆነ? ማንስ መረጠው? ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ ሥራ አመራር አካዳሚ ለምክር ቤት አባላት ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች በተሰጡበት ወቅት ምክር ቤቱን ወደ ሥራ ለማስገባት በማስፈለጉ ከየፓርቲዎቹ ሰዎችን የመለየት ሥራ እየተሰራ ነበር። በየፓርቲያችንም በተናጠል በመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ሰብስበውን ከአብን አንድ ሰው እንዲወከል ከመካከላችሁ አንድ ሰው ምረጡ የሚል ጥያቄ ቀረበልን። የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ የተከበሩ አቶ ዘመነ ኃይሉ፣ የተከበሩ አቶ ሙሉቀን አሰፋ፣ የተከበሩ አቶ አበባው ደሳለው እና እኔ ነን ተሰብሳቢዎቹ። ከአባላት መካከል የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የነበርሁ በመሆኑና ሌሎችንም የየራሳቸው መመዘኛዎች በመጠቀም እኔን በሙሉ ድምጽ መረጡኝ። የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆንኩበት መነሻም ይኸው ነው። ጥቅማ ጥቅሞችን በተመለከተ፤ በውሳኔ ቁጥር 43/2012 የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት መብቶችና ጥቅማጥቅም መመሪያ ላይ የተቀመጡ መብቶችና ጥቅማጥቅሞችን እንደማንኛውም የምክር ቤት አባልና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አገኛለሁ። ታዲያ ክርስቲያን የብልጽግና ፓርቲ የሥልጣን መጋራት ጥሪ ተቋዳሽ ነው የሚለው ከየት መጣ? እውነታው ይኼ ሆኖ እያሉ አንዳንዶች መረጃ ስለሌላቸው በየዋህነት፤ አንዳንዶች ደግሞ ከተራ ቅናትና ምቀኝነት በመሰል አሉባልታዎች ተጠምደዋል። እኔ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ አሁን በሰብሳቢነት የምመራውን የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊነት የተረከብሁት በሥልጣን መጋራት አይደለም። በወቅቱ ኃላፊነቱን የወሰድሁትም የምክር ቤት አባል ስለሆንሁ፤ ከገዥው ፓርቲ በመቀጠል አብላጫ ወንበር ያለውን አብን ስለወከልሁ፤ የራሴው አብን የምክር ቤት አባላት እንድወክላቸው ስለመረጡኝ እንጂ በሥልጣን መጋራት መንፈስ አይደለም። ይኼን እውነት በዚህ መልክ በአደባባይ ስናገርም ክብር፣ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል። ደግሞስ በሕዝብ ተመርጦ እንደራሴ ከመባል ወዲያ ምን ሹመት ሊመጣ ነው?!

Source: Link to the Post

Leave a Reply