You are currently viewing #የአብን ስራ አስፈፃሚ እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከሰሞኑ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባ ስለሆነው አሸናፊ አካሉ የሚከተለውን መረ…

#የአብን ስራ አስፈፃሚ እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከሰሞኑ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባ ስለሆነው አሸናፊ አካሉ የሚከተለውን መረ…

#የአብን ስራ አስፈፃሚ እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከሰሞኑ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰለባ ስለሆነው አሸናፊ አካሉ የሚከተለውን መረጃ አጋርተዋል። ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የይልቃል ከፋለ መንግስት የአብን የምዕራብ ጎጃም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን አሸናፊ አካሉ አስገድዶ ከሰወረው ከአስራ ምናምን ቀናት በኋላ ነገ በባሕር ዳር ከፍተኛ ፍርድቤት እንደሚያቀርበው ተሰምቷል። በዳኝነት ነፃነት ላይ ያለን የማይዛነፍ አክብሮት እንደተጠበቀ ሆኖ ችሎቱ በትግል ወንድማችን ላይ የተፈፀመበትን ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የይልቃል ከፋለን መንግስት የፀጥታ መዋቅር የውንብድና ድርጊት አጽንዖት ሰጥቶ ተገቢው ማብራሪያ እንዲሰጥበት ማድረግ ይኖርበታል። የአብን አባላትና ደጋፊዎች ለትግል ወንድማችን ያላችሁን አጋርነት ታሳዩ ዘንድም ጥሪ እናቀርባለን። (ለአባላቱና ደጋፊዎቹ ደኅንነት ግድ የሚለውን አብን በፍፁም መታደስ የሕዝብ፥ ለሕዝቡ፥ በሕዝቡ ሆኖ እንዲቀጥል በላቀ የኃላፊነት መንፈስ በአዲስ መነቃቃት እንድንቆምም ለንቅናቄው አባላትና ደጋፊዎች መልእክት እናስተላልፋለን።) አብን፥ የአዲሱ ትውልድ የዴሞክራሲ አምበል! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply