የአብን አስደንጋጭ መግለጫ!

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ****የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ድርጅታዊ ኅልውና ባገኘባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የአማራ ህዝብ እውነተኛ ድምፅ በመሆን ህዝባችንን ከኅልውና ስጋት ለመታደግ፣ አንድነቱን ለማረጋገጥና ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ የተቀጣጠለውን ንቅናቄ ጠንካራና የማይቀለበስ መሰረት በማስያዝ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽዖ አድርጓል። የአማራውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ኃብታዊ ጥያቄዎች ከፍ አድርጎ በመያዝና ለነፃነት፣ ለፍትኅና ለእኩልነት የሚደረገውን ትግል በመምራት ሕዝባዊ አመኔታን ለማትረፍ ችሏል፡፡ አብን ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ርእይ የሰነቀ ንቅናቄ በመሆኑ በአገራዊ የሽግግር ሂደት ውስጥ አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ …

Source: Link to the Post

Leave a Reply