
የአብይ መንግስት የአማራ ልጆችን እያፈነ የት እንደሚያደርሳቸው በህቅ ይጠየቅ! ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ወጣት ብስራት ካሳየ ይባላል። በደብርብርሃን ከመኖሪያ ቤቱ ከታፈነ ሁለተኛ ሳምንት እያስቆጠረ ነው ያለበት እስከ አሁን አይታወቅም። ባለቤቱና ልጆቹ እንዲሁም መላ ቤተሰቦቹ ያለበትን ማወቅ ይፈልጋሉ። ብስራት በአሸባሪው ህውሃት ወረራ ጊዜ የክልሉ መንግስት ክተት ሲል የፋኖ አደረጃጀትን በመቀላቀል የተዋደቀ በጦሳ ተራራ ደሴ ላይ እጁን የተመታና ከባድ ቁስለኛ ነው። ደሙን ለሃገሩ ያፈሰሰን የአማራን የቁርጥ ቀን ልጅ የአብይ አህመድ ግብረአበሮች አፍነው የት እንዳደረሱት እስከ አሁን አልታወቀም። ብስራት በጦርነት ወቅት በደረሰበት ጉዳት ቆስሎም ከነ ቁስሉ የተዋጋ ጀግንና እንጂ በካቴና የሚታሰር አይደለም። ብስራት እስከ አሁን ከእጁ ውስጥ ያልወጣ ብረት አለ። ቁስለኛ ነው። ህክምና ይፈልጋል። የአብይ መንግስት የት እንዳደረሰው እንዲያሳውቅ እየተጠየቀ ነው። ሁሉም መልክቱን ሸር በማድረግ ለብስራት ድምጽ ይሁን። በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸምን አፈና፤ ግድያ፤ ማሳደድ በጋራ እናስቁም! መንግስታዊ ሽብርና አፈና እና ግድያ ይቁም! ፍትህ ለብስራት! ፋትህ በግፈ ለታሰሩ፤ ለሚገደሉ የአማራ ልጆች! ፍትህ ለአማራ ህዝብ! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post