
የአብይ አህመድ አስተዳደር ሎተሪ አዟሪዎች አዲስ አበባ ውስጥ እንዳይሰሩ ክልከላ መጀመሩ ተገለፀ! መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እንደሚታወቀው ሎተሪ አዟሪዎች አብዛኛዎቹ ከልመና ሰርቶ መብላትን ምርጫ ያደረጉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች ሲሆኑ ፥ ሎተሪውን ከብሔራዊ ሎተሪ አለያ ደግሞ ፈቃድ ካላቸው አከፋፋዮች በመግዛት አዙረው እየሸጡ የእለት ጉርሳቸውን ያገኛሉ ፥ ኑሯቸውን ይደጉማሉ! ይሁን እንጂ ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ፥ ግፍ መስራትን መገለጫው ያደረገው የአብይ አስተዳደር ሎተሪ አዟሪዎችን << ፋኖ ናችሁ ፥ ለስለላ ነዉ የምትዞሩ ሰላዮች ናችሁ! >> የሚል የነውር ታፔላ በመለጠፍ ፥ አዟሪዎች በአዲስአበባ ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ የከለከለ ሲሆን ፥ ሲያዞሩ የተገኙትን ሎተሪያቸውን በመቀማት ለእስርና ለድብደባ እየዳረጉ መሆኑን የመንግስታዊ ግፉ ሰለባ የሆኑ ሎተሪ አዟሪዎች ገልፀዋል! የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት አዟሪዎች አያይዘውም ፥ << ሰላይ ፋኖ ናችሁ ከሚለው ፍረጃ ባሻገር እኛ ሎተሪ የምንረከበው ከአስተዳደሩ ቅርንጫፍ እና ፈቃድ ከተሰጠዉ አካል ሆኖ ሳለ ፥ የምንይዘዉ ሎተሪ በተቋሙ እዉቅና የለዉም ፥ ፎርጅድ ሎተሪ ነዉ የምታዞሩ እየተባልን ፥ በብሄራችን ብቻ እየተመረጥን ጥቃት ደርሶብናል። እባካችሁ ድምፅ ሁኑን! ሎተሪ አዙረን ለበላን ብሄራችን ታይቶ እየተሳደዱ መሆናቸውን የዘገበው አሚማ ነው ። "ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።" ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post