የአቶ በረከት ሴራ ብአዴንን ከማፍረስ እስከ ዶ/ር አብይ የጠ/ሚኒስትር ምርጫ (አያሌው መንበር)

ወቅቱ ታህሳስ ወር ላይ ገደማ ነው።ኢህአዴግ ተሀድሶውን ገምግሞ አቅጣጫ አስቀመጠ።አሁን ሀገርም ድርጅቱም ቀውስ ውስጥ ናቸው።በ17 ቀን ግምገማው ይህንን ቀውስ ለማለፍ 4ቱም ብሄራዊ ድርጅቶች ግምገማ ይቀመጡ ብሎ ወሰነ።ህወሃት 35 ቀናትን አሴረ፣ መከረ ዘከረ።

ብአዴንም እንዲሁ።.

የበረከት ሴራ 1፦አሁን ያለውን የብአዴን አመራር አብዛኛውን ባለፈው ጥር ወር ላይ መበተን

በዋናነት ብአዴንን በማሽከርከር የሚታወቁት እነ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ስምኦን፣ ታደሰ ካሳ፣ ከበደ ጫኔን ጨምሮ 11 የብአዴን አመራሮች አንድ ምክክር አደረጉ።ኢህአዴግ ምክር ቤት ላይ ለህወሀት እና ለዚህ ድርጅት አዳሪ የብአዴን አመራሮች ላይ ከፍተኛ ፈተና የሆኑትን ዶ/ር አምባቸው መኮነን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ደመቀ መኮነን፣ ተስፋየ ጌታቸው እና መሰል ወደ አማራ ህዝብ አዘንብለዋል የተባሉ አመራሮችን በሌላ መተካት የሚል።እነደመቀን በእነ ጌታቸው አምባየ የድርጅት ሊ/መንበር የማድረግ በኋላም ጠ/ሚኒስትርነቱን በኦህዴድ በማስያዝ ጌታየን ምክትል ለማድረግ አቅደው ከአዲስ አበባ ባህር ዳር በረሩ።

የዚህ እቅድ ፊታውራሪ አቶ በረከት ስምኦን ነበር።በዚህ ጊዜ ለመነሻነት ያቀረቡት ሀሳብ “በክልሉ የብሄር ግጭት እየተፈጠረ የሌላ ብሄር በሰላም የመኖር መብቱ ተነፍጓል፤ ይህንን ችግር ይህ አመራር ማስቆምና ክልሉን ማረጋጋት አይችልም” የሚል ነበር።ላይ ላይ ቅቡ ክልሉ አልተረጋጋም ነበርና እውነት ይመስላል።ውስጡ ግን መርዝ ያዘለ ነበር።በዚህ ጊዜ ታድያ ይህንን ተልዕኮ ከአዲስ አበባ ይዞ ባህር ዳር የከተመው ቡድን ያልጠበቀው ነገር ገጠመው።አቶ ደመቀ መኮነን ለአቶ በረከትና የተንኮል ልዑኩ እንዲህ አላቸው

<<እናንተ እኮ ድሮም ለአማራ ህዝብ የሚታገል አትፈልጉም>>አላቸው።ይህንን ጊዜ ታድያ የለውጥ ቡድን የሚባለው የብአዴን አመራር ይህንን ንግግር ሲሰማ እየተነሳ እነበረከትን ጠዘጠዛቸው።

በመጨረሻም የእነ በረከት የብአዴንን ስራ አስፈፃሚን የመበተን እና በአዲስ የማደራጀት ሃሳብ ከሸፈ።ይህ ሲከሽፍ ታድያ 11ዱ የብአዴን አመራሮች እነበረከትን ደግፈው በልዩነት ወጡ።ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ብአዴን ውስጥ የጎራ መከፋፈሉ በግልፅ ታየ።እንግዲህ ብአዴን ከመከረባቸው አጀንዳዎች አንዱ ይህ ሲሆን ሌሎች የአማራ ህዝብ ጉዳዮችም ተነስተው ነበር።

2.የበረከት ሴራ 2 በኢህአዴግ (ኦህዴድ) መንደር

በረከት እነ ብአዴን ላይ ማሸነፍ አልቻለም።ከዚህ በኋላ ወደአዲስ አበባ ተመለሰና ከአባዱላ ጋር መከረ።አባዱላን የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር የማድረግና የህወሃት ታዛዥ ለማድረግ ሌላ እቅድ ተያዘ።ምናሴም ፍንክንክ አለ።ይህንን ጊዜ ኦህዴድ የማዕከላዊ ኮሚቴውን ስብሰባ ባደረገ ማግስት ነበር መረጃው ለማ ጋር የደረሰው።በነገራችን ላይ ለለማ የነገረው ራሱ አባዱላ ነው ይባላል።ኦህዴድ በአስቸኳይ በሁለተኛው ቀን የማዕከላዊ ስብሰባ ጠራና ዶ/ር አብይን የድርጅቱ ሊ/መንበር አድርጎ መረጠ።ይህም ማለት የለውጥ ሀይሉ ቡድን እና ለህወሃት አይታዘዝም የሚባለውን መሪ አደረገ ማለት ነው።የበረከት ሁለተኛ ሴራ እዚህ ላይ ከሸፈ።..

3.የበረከት 3ኛ ሴራ በደኢህአዴን ውስጥ እና ከደኢህዴን ሾልኮ ብአዴን ውስጥ የደረሰው መረጃ

በረከት አሁንም አላረፈም።እጁረጅም ነውና ወደ ደኢህዴን ተሻገረ።ሀይለማሪያም ደበብ ሂዶ ሪዛይን እንዲያደርግና ሽፈራውን እንዲያስመርጥ ታቀደ።እነ ሲራጅ ፈጌሳም ተነገራቸው።የዚህ እቅድ ደግሞ አካሄዱ ብአዴንን የማፍረስ እቅድ ስለከሸፈ፣ አባዱላን ጠ/ሚ/ር ማድረግም ስለከሸፈ ሽፈራውን ጠ/ሚ/ር አድርጎ ሹሞ እንደፈለጉ ማዘዝ ነው።ደኢህዴን የስልጣን ጊዜየን አልጨረስኩም የሚል ሀሳብ እንዲያነሳም ታቀደ።በወቅቱ ታድያ አንድ ተጨማሩ መረጃ ወጣ።ብአዴንም ደመቀና ገዱን ይቀይራል ብለው እዛው አውሩና ከብአዴን ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራቸው የደኢህዴን አመራሮች ደመቀ ጋር ደውለው ይጠይቃሉ።ይህንን ጊዜ ታድያ እነ ደመቀም የበረከትን እና የህወሃትን አካሄድ ለማክሸፍ ሌላ ስልት ነደፉ።…

4.የበረከት ሴራ በጠ/ሚኒስትር ምርጫ ወቅት

ይህ ነጥብ ከሶስቱም ሴራዎች ጋር ትስስር አለው።ነገር ግን ነጥየ ያወጣውት በረከት የጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ ጥቆማውን ጉዳይ ሰው የማያውቅ መስሎት ህዝብ ላይ የፈጠረው ውዥንብርና ዶ/ር አብይና ደመቀን ለማለያየት (አይችልም እንጅ) የሄደበት ርቀት ስላስገረመኝ ሰፋ ለማድረግ ፈልጌ ነው።…በረከት የdismanteling (ነጥሎ የማዳከም) ፖለቲካ ፈላስፋ ነው።

የበረከት ተንኮል የጠ/ሚ/ር ምርጫ ጅምሩ ከአባዱላ ከዚያም ሽፈራው ሽጉጤ ጋር ይደርሳል።በረከት በሴራ እጅግ የተካነ ነው።ያው የመለስ ፎቶ ኮፒ ነው።የአባዱላ ጠ/ሚርነት ሲከሽፍበት በረከት ከደኢህዴና ህወሃት ጋር መነጋገርን መረጠ።በሂደትም የብአዴን Old guards እና ሁለቱ ድርጅቶች ለሽፈራው ድምፅ እንዲሰጡ፣ በበረከት እቅድ ጌታቸው አምባየን ምረጥ ተብሎ እምቢ ያለው ብአዴንም ደመቀን ለእጩነት ያቀርባል፣ ኦህዴድም አብይን ያቀርባል፣ ደኢህዴን ሽፈራውን ያቀርባል ከዚያም ህወሃት እና ደኢህዴን 90 ድምፅ ለሽፈራው ሲሰጡ፣ ብአዴን ለደመቀ ቢያንስ 35 ድምፅ ቢሰጥ፣ ኦህዴድ ለአብይ 45 ድምፅ ይሰጥና የኦህዴድና የብአዴን ድምፅ ሲከፋፈል ለሽፈራው እድል ይፈጥራል ከዚያም በረከት እና ህወሃት በዚያ ስልት ያሽከረክሩታል የሚል ነበር።በረከት ያው የዚህ ዘዴ መሀንዲስ ነው።

በዚህ ጊዜ ታድያ ብአዴን እና ኦህዴድ ሁለት መላ ዘየዱ።አስመራጭ ኮሚቴው የሰራውን ገራሚ ነገር ልጨምር።

1.በኢህአዴግ ህግ በምርጫ ወቅት የቀድሞ ተጋዮች ድምፅ ይሰጡ ነበር።በዚህ ጊዜ ታድያ አስመራጭ ኮሚቴው ይህንን ህግ እናሻሽለው የሚል ሀሳብ አቀረበና በድምፅ ብልጫ “ነባር ታዛቢ አመራሮች ድምፅ መስጠት እንዳይችሉ” የሚል ስምምነት ላይ ተደረሰ።ይህ የተንኮለኛውን ቡድን ድምፅ የፍናል ማለት ነው።ያም ሁኖ ግን ህወሃትና ደኢህዴን ብዙ ድምፅ ስላላቸው እና ቀድሞ የተሰራ ስራ ስላለ ይህንን ህግ ለማሻሻል ብዙ አልተቸገሩም።

2ኛው እና አስገራሚው ነገር በረከት አሁን የዋሸው ነገር ደግሞ ደመቀ፣ ተስፋየ፣ አምባቸውና ገዱ ብቻ ከምርጫው ከአንድ ቀን በፊት የሚያውቁት ደመቀ ከምርጫው ራሱን እንዲያገል ይህንን ጉዳይም መድረኩ ላይ ይፋ እንዲያደርግ የሚለው የውስጥ ስምምነት ነው።ሀሳቡ የመነጨው ከራሱ ከደመቀ ነው።ይህም ማለት ደመቀ ም/ጠ/ሚኒስትርነቱን ይዞ ይቀጥላል፤ ብአዴን እጩ አየቀርብም፣ ለአብይ ብአዴንን ጨምሮ ከ85 በላይ ድምፅ ይሰጣል ማለት ነው።ይህንን እቅድ እነ በረከት አያውቁትም ነበር።ብአዴን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ሁኔታ እነበረከትና ህወሃትን አታለለ።ይህንን ሀሳብ ለእነ ለማ አሳውቀው በውስጥ ለውስጥ ደመቀ እንደማይወዳደር ይጠቅሙኛል ላሏቸው የብአዴን አመራሮች ነግረው በምትኩ አብይን እንዲመርጡ መከሩ።

ደመቀም ይህንን ውሳኔ በውስጡ ይዞ መድረክ ላይ መወዳደር እንደማይፈልግ፣ ድርጅቱም እጩ እንደማያቀርብ ይፋ አደረገ።ከዚያም እነበረከት ደነገጡ።የሽፈራው አለመመረጥ ያን ጊዜ ተረጋገጠ።በረከት በዚህም ላይ አላቆመም።ደመቀ ምክትልነቱን እንዳለ መያዝ አይችልም።ስለዚህ ምክትሉ ቦታም በውድድር ይሁን ብሎ አነሳ።በዚህን ጊዜ ከዚህ በፊትም መለስ ሲሞት አዲስ አሰራር ስላልተከተልን፣ መመሪያውም ስለማያግድ፣ የተሰበሰብነውም ሊ/መንበር ለመምረጥ እንጅ ምክትል ለመምረጥ ስላልሆነ ሀሳቡ ተቀባይነት የለውም በማለት ደመቀ ራሱ ወደ ውይይት ሳይዘረጋ ደመደመው።ሁሉም ተስማማ።

አሁን ወደ ጥቆማ ተገባ።ለማ አብይን ጠቆሞ።የብአዴን ሰው ለተንኮል ደብረጽዮንን ጠቆመ።ደኢህዴድንም ሽፈራንው ጠቆመ።.በተጠቋሚዎች ላይ አስተያየት ሲባል፦-

በረከት አብይን ለማስጠላት እንዲህ አለ፦ “አብይ አባዱላን ያመዋል፣ አባዱላ የምርኮ አስተሳሰብ ያለው ደርግ ነው ብሎኛል” ሲል አብይ ደግሞ “ይሄ የወረደ እና ተራ አሉሽ አሉሽ ነው በማለት የበረከትን ሀሳብ አጣጣለ።

የበረከት ግርፍና ቀድሞ ቃል ተገብቶለት የከሸፈበት ጌታቸው አምባየም “እኔም በአብይ ላይ ማስረጃ አለኝ ሙሰኛ ነው” በማለት አቀረበ።.

ሁለቱም ሀሳብ ተሰጠባቸውና ወደ ምርጫ ተገባ።ብአዴንና ኦህዴድ አብይን ሲመርጡ ከፊል ደኢህዴንና ህወሃት ሽፈራውን መረጡ።ያው ደብረጽዮን ለውክልና ስለገባ ሁለት ድምፅ ይመስለኛል ይዞ ወጣ።

እንግዲህ በረከት ስለደመቀ ትናንት ሲያወራ “ጠ/ሚኒስትር ሳትመርጠኝ” ብሎ የሚለው በአንድ በኩል ደመቀ ቀድሞ ራሱን ከውድድር ውጭ ያደረገውን እንደማያውቅ እየዋሸን ነው።በሌላ በኩል ደግሞ አብይ እንዳይመረጥ የሰጠውን ሀሳብም ሰው መቸም አይሰማም ብሎ ነው።አብይን ለማስጠላት በአባዱላ ላይ የሰራውን ነገር አሁን ደግሞ አብይና ደመቀን ለመነጠል በሚመስል መልኩ ሲጓዝ ተመለከትነው።…

ዳሩ ግን የበረከት የሰሞኑ አካሄድ ውሸታምና ሴረኛነቱን የበለጠ ነው ያጋለጠ። ለአብይና ለደመቀም ምንም እንኳን የሚያውቁት ቢሆን የበለጠ ራሱን ነው የገለጠላቸው።ለህዝብም ጭምር።.በረከት ማለት ይህ ነው።

Leave a Reply