የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት ያነሳው 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ነው፡፡

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፓርላማ የገቡት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ወክለው ተወዳድረው ነው።

አቶ ክርስቲያን ፓርላማ ከገቡ በኋላ በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዋል።

ሆኖም በአማራ ክልል የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ባለፈው ሐምሌ ወር በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ላላፉት ሰባት ወራት በእስር ላይ ይገኛሉ።

አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ስር ከዋሉ ከሰባት ወራት በኋላ ነው ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸውን የተነሳው፡፡

ከአቶ ክርስቲያን በተጨማሪ ሌላኛው የአብን ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔም ባለፈው ጥር መጨረሻ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply