የአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማትን በማስፋፋት ፍትሃዊ፤ ዘለቄታዊና ተስማሚ የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ

የአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማትን በማስፋፋት ፍትሃዊ፤ ዘለቄታዊና ተስማሚ የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማትን በማስፋፋትና መዋቅራዊ ሽግግሩን በማፋጠን ፍትሃዊ፤ ዘለቄታዊና ተስማሚ የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የፌዴራል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአነስተኛና መካከለኛ ማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ዙሪያ ከሀረሪ ክልል እና ከድሬዳዋ መስተዳድር የካቢኔ አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለጹት የአነስተኛና መካከለኛ ማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማትን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር የትስስር ስርአትን በመዘርጋት ከአደረጃጀት፤ ከአሰራርና ከህግ ማእቀፍ ጋር ተያይዞ ምቹ የስራ ሁኔታን መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ እንደገለጹት የአነስተኛና መካከለኛ ማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማትን በማስፋፋትና መዋቅራዊ ሽግግሩን በማፋጠን ፍትሃዊ፤ ዘለቄታዊና ውጤታማ የስራ እድል በመፍጠር የሐገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ዋና አላማም በሀገሪቱ የስራ መዋቅራዊ ለውጥን በማምጣትና እሴትን በመጨመር የወጣቱን የስራ ተነሳሽነትን በማሳደግ የሀገርን ኢኮኖሚ መገንባት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በበኩላቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች ለኢትዮጵያ የኢንደስትሪ እድገትና ልማት መሰረት ለመጣል ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡

ክልሎች የስራ እድል ፈጠራንና የስራ ባህልን ለማሳደግ እንዲያስችላቸው ባለፈው አመት ከተመደው 4.7 ቢሊዮን በጀት ውስጥ 1.8 ሚሊዮን ወይንም 40 በመቶው ብቻ ስራ ላይ መዋሉን አስታውቀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የአነስተኛና መካከለኛ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ልማትን በማስፋፋት ፍትሃዊ፤ ዘለቄታዊና ተስማሚ የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply