የአንበጣ መንጋን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል ግብረ-ኃይል በማቋቋም እየሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒሰቴር መሰሪያ ቤቱ የአንበጣ መንጋን አስቀድሞ ለመከላከልና ተባዮች በደረሰ ሰብል ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን ገልጻዋል፡፡የግብርና ሚኒስቴር የዕጽዋት ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ ለአሐዱ እንደተናገሩት የበርሃ አንበጣ ዳግም እንዳይራባ ቦታዎችን በመለየት በ13 አውሮፕላን እና በመኪናዎች በመታገዝ የቅድመ መከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአንበጣ መንጋን አስቀድሞ ለመከላለከል የሚያስችል ግብረ-ኃይል በማቋቋም ስልጠና መሰጠቱን የተናገሩት አቶ በላይነህ የደቡብ አካባቢ ደረቃማ በመሆኑ የመራባት ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል በሚል ተባዮችን ለማጥፋትና ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡም የደረሰ ሰብልም ይሁን መስኖ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

*****************************************************************************

ቀን 18/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post የአንበጣ መንጋን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል ግብረ-ኃይል በማቋቋም እየሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply