የአንድ ቀን ዕለታዊ ወጪን ለአገር መከላከያ ሰራዊት

መላው ኢትዮጵያዊ የሚሳተፍበት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ሊያከናውን መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

መርሃ ግብሩ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የሚከናወን ሲሆን “ጥበብ ለእናት አገር” እንደሚሰኝም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያዊያን የአንድ ቀን ዕለታዊ ወጪያቸውን ለመከላከያ ሰራዊት በተከፈተው የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አካውንት እንዲለግሱም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሚኒስቴሩ በዋናነት ለመከላከያ ሰራዊት ስንቅ እንደሚያዘጋጅ ፣ ደም እንደሚለግስ፣ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ እንደሚያሰባስብ እና በጦርነቱ ቆስለው በሆስፒታል የሚገኙ የሰራዊቱ አባላትን እንደሚጎበኝ የሚኒስቴሩ የኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ የፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አል ማሃዲ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ይቀርባሉ ነው ያሉት፡፡

በመርሀ ግብሩ ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር የሙዚቀኞች፣ የአርቲስቶች እና ሰዓሊያን ማህበራት እንደሚሳተፉበት ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ኅዳር 26 በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በተከፈተ የባንክ አካውንት “ዛሬን ለሀገሬ” በተባለ ሕዝባዊ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች የኪነጥበብ ባለሙያዎች በማስተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡

ቀን 23/03/2014

አሐዱ ቴሌቪዥን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply