የአንድ ወር የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ተጀመረ

የአንድ ወር የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥቅምት 9 እስከ ኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆየው የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

በዘመቻው ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረም በተቻለ መጠንና በዘላቂነት እንደሚወገድ ይጠበቃል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዘመቻው ማስጀመሪያ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በዚህ ንቅናቄ ተሳታፊ እንዲሆን በክልሉ መንግስት ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

The post የአንድ ወር የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ተጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply