You are currently viewing የአንገር ጉትን አማራዎችን ማሰሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ በአንገር ጉትን ከተማ የኦሮሚታ ልዩ…

የአንገር ጉትን አማራዎችን ማሰሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአንገር ጉትን ከተማ የኦሮሚታ ልዩ…

የአንገር ጉትን አማራዎችን ማሰሩ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአንገር ጉትን ከተማ የኦሮሚታ ልዩ ኃይሎችና የኦሮሞ ሚሊሾች ከመከላከያን ጋር በመሆን የግል ታጣቂዎችን ይኸ መሳሪያ አለው፤ ይሔ በውጊያው ተሳትፏል፤ ተዋግቷል እያሉ በጥቆማ እያስያዙ ነዉ። አሁን በዚህ ሰዓት ማለትም 01-04-2015 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ላይ ከ15 ቁጥር 4 ሰዎችን በማስያዝ ፖሊስ ጣቢያ አስወስደዋል። ከነዚህም መካከልም፦ 1- ፍሰሀ ሞላልኝ፣ 2- ጫኔ ገዳሙ፣ 3- ሞገስ እና 4- ታረቀኝ የሚባሉ ናቸው፤ አሁንም እያሳደዱ በመያዝ ላይ ናቸው። ይህ በእንድህ እንዳለ ሌሎች የጉትን ከተማ ሚሊሻዎችን በመሰብሰብ መሳሪያ እንዲያወርዱ በማድረግ ላይ በመሆናቸው ከተማው ዳግም ወደ ውጥረት እየገባ መሆኑን ምንጮች ስለመናገራቸው የአጉልዞ ዘገባ አመልክቷል። ከህዳር 25/2015 ጀምሮ ወደ ነቀምት የተላለፈውን ሙሉቀን አንተነህን ጨምሮ ከ17 በላይ የሚሆኑ ጠንካራ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች በመከላከያ እየተያዙ ለፖሊስበተላልፈው ስለመሰጠታቸው ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply