You are currently viewing የአንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታወቀ፤ በከተማው የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ገደቡን ፍትሃዊነት የጎደለው ሲሉ አውግዘውታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

የአንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታወቀ፤ በከተማው የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ገደቡን ፍትሃዊነት የጎደለው ሲሉ አውግዘውታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

የአንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታወቀ፤ በከተማው የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ገደቡን ፍትሃዊነት የጎደለው ሲሉ አውግዘውታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለው በከተማዋ አስጊ ሁኔታ ስላለነው በማለት መስተዳድሩ ገልጧል። በዚህም ከመጋቢት 26/2015ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት 12:00 ሰዓት ድረስ የሰዓት እላፊ ገደብ ተላልፏል። ይህን ገደብ ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን መልዕክቱን በድምፅ ማጉያ አስተላልፏል። የሰዓት እላፊ ገደቡ ሙስሊሞች የሮመዳንን ጾም መስጊድ ሄደው በነጻነት እንዳይሰግዱ ለማድረግ ያለመ ነው በሚል መስተዳድሩ ተወቅሷል፤ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ተጠይቋል። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ አራት ሰዓት ድረስ በመስጊድ መቆዬት ግድ እንደሚልም ተመላክቷል። ለዘገባው አጉልዞ ጥያቄን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply