የአንጋፋው የስነጽሁፍ መምህር ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው የቀብር ስነ ስርዓት በነገው እለት ይፈጸማል።በሥነ ጽሁፍ ዘርፍ በመምህርነት ከሚጠቀሡት ጉምቱ ሰዎች መካከል ዋነኛ የሆኑትና የአዲስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/pcG_X-hY48pnO_jOptLl56K8dWRr-OejYSHgYlKUMmaOgXLMJxWXuEhc5aEWuRHj_JLG_Ne1LQ9eWlST4MEdt9hDHQWl6eA9d9F3G_9fJsy5i51rTP5wI3-gUUy0-i6lmTj6bbGTuBmyvqyUsnpB_ClyeOVUwwqzh1VUafK9K3WJM82GTitAmgKWzohZJz9djx6TBjQVg4zENEqOF5nKghnuFl_PCqDyUzxTd4TqNo3PrrKSNkdkIWkD2O2uhQNw88KqPp2H-R1_1I2G8MVo7GATGXPeyFBi3-xeKPCv5uas11XIGLspwm6ZuX12lHV3QDTQeq7Mf0qAzAehZtriNg.jpg

የአንጋፋው የስነጽሁፍ መምህር ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው የቀብር ስነ ስርዓት በነገው እለት ይፈጸማል።

በሥነ ጽሁፍ ዘርፍ በመምህርነት ከሚጠቀሡት ጉምቱ ሰዎች መካከል ዋነኛ የሆኑትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ መምህር የነበሩት ተ/ ፕሮፌሠር ዘሪሁን አስፋው ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሥነጽሑፍን ያስተማሩና የአማርኛ ሥነጽሑፍ ታሪክን እና ቴክኒክን ያጠኑ ናቸው::

የስነፅሁፍ መሠረታውያን እና ‘ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ’ በሚሉ መፅሐፎቻቸውም ይታወቃሉ::

ሰሞኑን ለፍቅር እስከመቃብር የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ጥናት እንዲያቀርቡ ከተመረጡት አንዱ ጋሽ ዘሪሁን ነበሩ።

በፍቅር እስከመቃብር መጽሐፍ ዙሪያ ጥልቅ ጥናት አድርገዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን ከትምህርቱ ዘርፍ በተጨማሪ ከፖፑሌየሽን ሚዲያ ሴንተር ጋር በመሆን የተለያዩ የሥነ ሕዝብ ጥናቶችን የሰሩ ሲሆን፣ ወጣት ደራሲያን እና ተመራማሪዎችን በማማከር እና በመደገፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል::

ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን በማስተማር ሥራቸው ብቻ ሳይሆን በጥናት እና ምርምር ሥራዎች ላይ”የኢትዮጵያን ሥነጽሑፍ የሰነዱ” ታላቅ መምህር ነበሩ።

እኝህ አንጋፋ መምህር ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 28 2015 ዓ.ም ማረፋቸው ተሰምቷል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነገ ከቀኑ 9፡00 በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply