የአንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ

የአንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ፡፡
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዛሬ ቤተሰቦቹ፣ ዘመድ አዝማዶቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ በተገኙበት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በድጋሚ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡
አርቲስት አየለ ማሞ ከዜማና ግጥም ደራሲነቱ ባለፈም የማንዶሊኑ ንጉስ በመባል ይታወቃል፡፡
አርቲስት አየለ ለአንጋፋ ድምጻውያን በርካታ ዜማዎችን ሰርቶ ከመስጠት ባለፈ ወይ ካሊፕሶ በሚለው ሙዚቃ በህዝብ ዘንድ ይበልጥ እውቅናን አግኝቷል፡፡
እንዲሁም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ1950ዎቹ ጀምሮ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ አንጋፋ ባለሙያም ነበር፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የአንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply