You are currently viewing የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የበኩር ልጅ የሙሴ ደምስ አስከሬን የፊታችን ቅዳሜ ጥር 7 ቀን ወደ አዲስ አበባ ይገባል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም       አዲ…

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የበኩር ልጅ የሙሴ ደምስ አስከሬን የፊታችን ቅዳሜ ጥር 7 ቀን ወደ አዲስ አበባ ይገባል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲ…

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የበኩር ልጅ የሙሴ ደምስ አስከሬን የፊታችን ቅዳሜ ጥር 7 ቀን ወደ አዲስ አበባ ይገባል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እዮኤል ሙሴ የተባለ የ17 ዓመት ልጅ አባት የሆነው የ36 ዓመቱ ጎልማሳ ሙሴ ደምስ የጀግና አባቱን የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠን ፈለግ የተከተለ ፍትህ እና ለውጥ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ለውጥ እንዲመጣም እየታገለ የነበረ ብርቱ ሰው ስለመሆኑ ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። የአንጋፋው ጋዜጠኛ፣ አርበኛ እና የጥበብ ሰው ደምስ በለጠ አሟሟት ቤተሰቡን ጨምሮ ለብዙዎች የማይሽር የውስጥ ህመም መሆኑ ሳያንስ የበኩር ልጃቸው ሙሴ ደምስ በለጠ December 29, 2021_ታህሳስ 20 ቀን 2014 በዋሸንግተን ዲሲ ባልታወቁ ሰዎች በደረስበት ጥቃት ህይወቱ የማለፉን ዜና መስማት አሳዛኝ ነበር፡፡ የሙሴ ደምስ አስከሬንም የፊታችን ቅዳሜ ጥር 7 ቀን 2014 ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ይገባል፤ በቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን በአባቱ በጋዜጠኛ ደምስ በለጠ መቃብር ጎን ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም አሚማ ከቤተሰብ ያገኘው መረጃ አመልክቷል። ሂደቱም ቅዳሜ ጠዋት አስከሬኑ አዲስ አበባ እንደገባ በቀጥታ ወደ መነን አካባቢ መኖሪያ ቤት ይወሰዳል፤ ከዛም ጸሎትና ፍትሃት ይደረግለታል፤ በመቀጠልም ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ስርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል። ሀገራዊ ስም አወጣጥ የሚችሉት አንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ከበኩር ልጃቸው ከሙሴ በተጨማሪ ዜማ፣ምኒልክ፣ገላውዲዎስ የተባሉ ልጆች አሏቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply