የአከራይና ተከራይ ምዝገባ ሰኔ 30 የሚጠናቀቅ ሲሆን ያልተመዘገቡ የቤት አከራዮች ከ2 እስከ 3 ወራት የቤት ኪራይ ገቢያቸውን ይቀጣሉ 

ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ጀምሮ ተፈጻሚ መሆን የጀመረው የቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን ተከትሎ እስከ ሰኔ 30 ድረስ በወረዳ ቀርበው የማይመዘገቡ አከራዮች እንደሚቀጡ በአዋጁ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀው በየወረዳው የአከራይ እና ተከራይ ምዝገባ እየተካሄደ ሲሆን በቀሪዎቹ 15 ቀናት ውስጥ ያልተመዘገቡ አከራዮች፤ ሳይመዘገብ እስከ ሶስት ወራት የሚቆዩ የሁለት ወራት ቤት ኪራይና ከሶስት ወራት በላይ የቆዩና ምዝገባ ሳያደርጉ በተቆጣጣሪ አካል አሰሳ የሚገኙ ደግሞ የሶስት ወራት የቤት ኪራይ እንደሚቀጡ ተገልጿል።

ምዝገባው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከጠዋት እስከ ምሽት እየተከናወነ ሲሆን ቤት አከራዮች ሕጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽህፈት ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት የቤት ባለቤትነት አልያም ሕጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተከራዮች ደግሞ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ወይንም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply