You are currently viewing ” የአኩሪዋ ፣ ጥቁር ኮኮብ ሐገር ፣ ንጉሰነገስት ”                    (ክፍል አንድ )      ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) የካ…

” የአኩሪዋ ፣ ጥቁር ኮኮብ ሐገር ፣ ንጉሰነገስት ” (ክፍል አንድ ) ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) የካ…

” የአኩሪዋ ፣ ጥቁር ኮኮብ ሐገር ፣ ንጉሰነገስት ” (ክፍል አንድ ) ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባቡሩም ሰገረ…….. ስልኩም ተናገረ ፣ ይህ በማን ግዜ…….. ተደርጎ ነበረ ፣ ምንይልክ ነብይ …….. ነው ሆዴ ጠረጠረ :: እንደምን አላችሁልኝ ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ :: ለዛሬው : የጥቁሩን ሱናሜ : መሪ : የኢትዮጵያን ንጉሰነገስት መንግስት በአለም የወርቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን ስለፃፉት ገናና የእምዬ ምንይልክ ታሪክ ይህው ክፍል አንድን ጀመርኩ :: ዛሬ ከደረስንበት: የዘመነ ሮበት ደረጃ :ላይ ሆነን :የቀድሞ አባቶችንን የስልጣኔ ፍቅርና : ምኞት : ምን ያህል እንደነበረ ስናጤንው : ለሐገራቸውና :ለህዝባቸው ሲሰሩት : የነበረውን ድካም: መስፈርቱን መለካት ያቅተናል :: እነዚህን መሰል ቀደምት ፣ አባቶቻችን ያን ግዜ : ሲመኙት የነበረው ህልማቸው : እውን ሆኖ ሳያዩት : አፈር ትቢያ ሆነው በዩ ቤተክርስቲያኑ ታዛ ወድቀው : ቀርተዋል :: ነገርግን እንድሸክላ ዱቄት ሆኖ የፈራርሰው አካላቸው ሲሆን: አፈር የማያበላሸው ታሪካቸውን: ስናገላብጥ የምናገኜው ምስክርነት :ለመንፈሳችን ነፃነት ለአላማችን ፅናት ይሰጠናል :: ለዛሬው ስለታላቁ የአድዋው የጦር መሪ የኢትዮጵያ ንጉሰነገስት መንግስት የነበሩትን እምዬ ምንይልክን እንስታውሳቸው አለን :: ሆኖም ግን ተጨልፎ የማያልቅ ባህር የሆነ ታሪክ ያላቸውን ምንይልክን የመሰለ ገናና ንጉሰንገስት እንደዚህ ነበሩ ብሎ በአጭር አቀራረብ ለመግለፅ ድካሙ የሰማይ ያህል እንደሚርቅ ወገኖቼ እንደምትገነዘቡልኝ አምናለሁ :: የምዬ ምንይልክ ታሪክ ብዛቱ በህዋው ላይ የፈሰሰን ኮኮብ ከመቁጠር አይተናነስም :: ለግዜው ግን ነጋድራስ አፈወርቅ ገ/እየሱስ ፣ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ዳኛቸው ወልደ /ስላሴ ፣ተክለፃዽቅ መኩሪያ ፣ፓውሎስ ኞኞ በተራራቁ አመተ ምህረቶች የፅፏቸውን የታሪክ መፃህፍቶች በትዕግስትና በብቃት መፈተሽ ግድ ይላል :: በዚህ ምክኒያት በእጄ ገብተው ያገኘዃቸውን የታሪክ ድርሳናትን አገላብጨ ቁምነገሮቹን ብቻ መርጨ ለውድ ወዳጆቼ ላካፍላችሁ ወደድኩ :: እምዬ ምንይሊክ በ1836 ዓ/ም ነሐሴ 12ቀን ቅዳሜ ከአባታቸው ከኃይለመለኮት ሣህለ ስላሴ ከናታቸው ከወ/ሮ እጅጋየሁ ለማ አድያሞ የተወለዱት ንጉስነገስት አፄ ምንይልክ ፣በአባታቸው የንጉስ ሳህለስላሴ፣ የልጅ ልጅ፣ የኃይለመለኮት ሳህለ ስላሴ ልጅ፣ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ፣ የንጉስ ሳህለስላሴ ፣ ሚስት የወ/ሮ በዛብሽ ሰራተኛ ናቸው :: የእጅጋየሁንም መውለድ ፣ንጉስ ሳህለ ስላሴ ሲሰሙ፣ የልጁን ስም “ምን ይልህ ሸዋ ” በሉት ብለው ስም አወጡለት :: ምን ይልህ ሸዋ ያሉበትም ምክኒያት ፣ የኔ ልጅ ኃይለመለኮት ከገረድ በመውለዱ ሸዋ ሲሰማ ፣ምን ይል ይሆን ? ለማለት ነው ይባላል :: በዃላ ግን በህልማቸው፣ ከምን ይልህ ፣ ሸዋ ጋር አብረው ቁመው ከእሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፣ በእግር የረገጡት መሬት፣ ሲያለካኩት እሳቸው ከረገጡት ፣ ልጁ የረገጠው ረዝሞ ተመክለከቱ :: ይህን ህልም ካዩ በዃላም፣ ምንይልክ የኔ ስም ሳይሆን የሱ ስም ነው :: ስሙን ምንይልክ ፣ በሉት ብለው በማዘዛቸው ምንይልክ ተባሉ :: ይህንም ያሉበት ምክኒያት ምንይልክ፣ በሚል በሚል ስም የሚነግስ ንጉስ ፣ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል ፣የሚል ትንቢት ስለነበር ሳህለ ስላሴ ሲነግሱ ፣ ስሜ ምንይልክ ይሁን ብለው ነበር :: ነገር ግን አንድ መነኩሴ ፣ በዚህ ስም አትንገስ ፣መጥፎ አጋጣሚ ይመጣብሀል ይሕ ስም የሚስማማው ፣ ከመጀመሪያው ወንድ ልጅህ ከሀይለመለኮት ፣ ለሚወለደው ነው :: ይህም ስም የሚወጣለት የልጅህ ልጅ ኢትዮጵያን አንድ ፣የሚያደርግ ትልቅ ንጉስ ይሆናል: አሏቸው : ይባላል :: በዚህ ምክኒያት የምንይልህ ሸዋ ስም ተቀይሮ ምንይልክ ተባሉ ሲል ” ክብረ ነገስት “ያትተዋል :: ህርበርት የተባለው ፀሐፊ ስለ ምንይልክ ሰውነት ሲገልፅ እንዲህ ይላል :: ምንይልክ ጥርሶቻቸው ግጥም ያሉ ነጫጮች ናቸው ::ትንንሽ አይኖቻቸው ደስ ይላሉ ፣ የአይኖቻቸው ውስጥም ከነጭነት ይልቅ ወደ ቢጫነት ያደላሉ ፣ግንባራቸው ጠባብ ነው ፣ትኩር ብለው ሲያዋቸው ደግና የተለያዬ ጠባዮች ያሏቸው መሆናቸውን ፊታቸው ያስታውቃል :: ጢምና ሪዛቸው የተጠጋጋ ቢሆንም ግራጫ ሁነዋል ፣ አነጋገራቸው እንደሌላው አበሻ ሁሉ ረጋ ያለ ነው :: ሲናገሩም ምላስና ጥርሳቸው ይታያል ፣ሲያዳምጡም ደግሞ ራሳቸውን መነቅነቅ ይወዳሉ :: ሲጫወቱ እጃቸውን አያወራጩም ፣አንዳንድ ጊዜ ብቻ ጣታቸውን ይደራርባሉ :: ሁል ጊዜ ፈገግተኛ ናቸው :: የመወደድ ጠባይ አላቸው ይህም ቢሆን ሲስቁ የሰሟቸው ወይንም ያዩዋቸው ሰዎች ጥቂቶች ናቸው ይላል :: ኮንት ግሊኮን በበኩሉ በርዝማኔ ከጫማቸው ሌላ 6ጫማ ይሆናሉ :: ምንይልክ ጠንካራ አቅም አላቸው፣ ቆዳቸው ጥቁር ነው :: አጠር ያለ ጢምና ሪዝ አላቸው ፣ ፊታቸው ከባድ ነው አስተያዬታቸው የጨዋ አስተያዬት ነው :: ፈገግታቸው ማራኪ ነው ፈገግ ሲሉም ውብ ጥርሶቻቸው ይታያሉ :: አዘውትረው ግንባራቸው ላይ ከምትታሰረው ሻሽ ላይ በወርቅ የተዘመዘመ ጥቁር ካባ ይደርባሉ :: በማለት ገለፃውን ሲያጠቃልል ሌላው የዘመኑ ፀሐፊ ቸያረኒ ፣ ምንይልክ ጨዋና የጦር መሳሪያ የሚወዱ ሰው ናቸው ሲናገሩም ረጋ ብለውና አስበው ነው :: ሲያዳምጡም በፀጥታ ነው :: ጥሩ ወታደር በመሆናቸው የጦር መሳሪያ መያዝ ይወዳሉ ::ቁመታቸው መካከለኛ ሆኖ ጡንቻቸው የፈረጠመ ነው :: ፊታቸው በፈንጣጣ ምክኒያት ተጉረብርቧል ::ግንባራቸው ሰፊ ነው :: እንዳፋቸው ሁሉ ደስ የሚሉ ጨዋ አይኖች አሏቸው :: አፍንጫቸው ትክክለኛ ሲሆን አገጫቸው ግን ትልቅ ነው :: ጥርሳቸው ትክክል ሆኖ የወጣና ነጭ ነው ሲል ፅሁፉን አጠቃሏል :: እኔም ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ :: ክፍል ሁለት ይዤ እስከምመለስ ቸር ይግጠመን :: አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply