የአካል ጉዳተኛችን የምርጫ ተሳትፎ ለማሳደግ ከ1ሺ 400 በላይ የምርጫ ቦርድ ህግና መመሪያ ቅጂ በብሬል እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡

አካል ጉዳተኞች በምርጫ ታዛቢነት፣ ተወዳዳሪነትና በመምረጥ መመረጥ ተሳትፏቸው እንዲጨምር ቦርዱ በትኩረት እየሰራው ነው ብሏል፡፡የምርጫ ቦርድ መመሪያ ቅጂ በብሬል፣ በድምጽና በምስል እያዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡ከአካል ጉዳተኞች ባለፈ ሴቶችም በምርጫ ታዛቢነት የሚኖራቸው ተሳትፎ ጠንካራ እንዲሆን የስርዓተ ጾታ ስብጥር ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ብዙወርቅ ከተተ ተናግረዋል፡፡ከ2መቶ ሺ በላይ ሰዎች ለምርጫ ታዛቢነት የተመለመሉ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጡረተኞችና ሴቶች መካተታው ታውቋል፡፡

በ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ከ54 ሺ 389 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተገለጸ ሲሆን ከ55 ሺ በላይ ታብሌቶች ለምርጫው ውጤት በተለያዩ ቦታዎች ለማስፈፀም ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል፡፡በምርጫ ሂደት ከዚህ ቀደም የነበሩ ኋላ ቀር አሰራሮችን በማስቀረት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከላፉት ምርጫዎች ልዩ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጻል፡፡

****************************************************************************

ቀን 17/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply