You are currently viewing የአክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃን የተሳሳተ ትርክት ሲፈተሽ! አሻራ ሚዲያ  ሰሜን አሜሪካ  በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በእጅጉ ከሚያስገርሙኝ ነገሮች ሁሉ የትግራይ እና የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃን…

የአክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃን የተሳሳተ ትርክት ሲፈተሽ! አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በእጅጉ ከሚያስገርሙኝ ነገሮች ሁሉ የትግራይ እና የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃን…

የአክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃን የተሳሳተ ትርክት ሲፈተሽ! አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በእጅጉ ከሚያስገርሙኝ ነገሮች ሁሉ የትግራይ እና የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃን እና ፖለቲከኞች አመላካከት፣ አስተሳሰብና አካሄድ አንድ የመሆኑ ጉዳይ ነው። በተለይም በአማራ ሕዝብና መሪዎች ላይ ያላቸው አቋም በእጅጉ የተንሸዋረረ ከመሆኑም በላይ በሚገርም ሁኔታ አንድና ተመሳሳይ የሆነ አተያይ አላቸው። በዚህ ረገድ ሦስት ምሳሌዎችን ማንሳት እችላለሁ፣ ከእነዚህ ውስጥ አንደኛውና የመጀመሪያው በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ ያላቸው የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን የተንሸዋረረ አተያይ ሲሆን ሁለቱም ልሂቃን በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ ያላቸው ጥላቻ እአጅጉ ቅጥ ያጣ መሆኑ ነው። ሁለቱም ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ለመጥላትና በጠላትነት ለመፈረጅ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ቅሬታ የውሸት በመሆኑ ማንንም አያሳምንም። በዚህ ረገድ ትግራዮቹ አክራሪ ብሔረተኛ ልሂቃንና ፖለቲከኞች ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ኤርትራን ለጣሊያን አሳልፎ በመስጠቱ ምክንያት ለሁለት ከፍሎናል በማለት ይከሳሉ። እውነታው ግን እነሱ ከሚሉት በፍጹም የተሐየ መሆኑ ነው። ኤርትራ በጣሊያን የተያዘችው በአጼ ዮሀንስ 4ኛ የአገዛዝ ዘመን ማለትም በ1879 ዓ.ም ሲሆን ይህም የሆነው ራስ አሉላ ዶጋሌ ላይ የጣሊያንን ጦር ወግተው በማሸነፋቸው የጣሊያን ወኪል አጼ ዮሀንስ 4ኛን በመወቀሱ እንደሆነ ይነገራል። በዛ ላይ አጼ ዮሀንስ 4ኛ የራስ አሉላን ጀግንነትና ሀይለኝነት ይፈሩት ስለነበረ ይህን ወቀሳ እንደ ሰበብ በመጠቀም ራስ አሉላን ከባህረ ነጋሽ (ኤርትራ) ገዥነት አንስተው ወደ ተንቤን በማምጣት በግዞት መልክ እንዲቀመጥ በማድረጉ ነው። በዚህ ወቅት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የሸዋ ንጉስ እንነበር ይታወቃል፤ አጼ ዮሀንስ 4ኛ በ1881 ዓ.ም መተማ ላይ ሲዋጋ በሱዳን ሀይሎች ተማርኮ ከተገደለ በኋላ ክፍተት ተፈጠረ። ይህን የአመራር ክፍተት ለመሙላት የትግራይ መሳፍንትና መኳንንት እርስ በርስ መስማማት ባለመቻላቸው ነጉሰ ነገስት መሰየም ሳይችሉ ቀሩና የሸዋ ንጉስ የነበሩት እምየ ምኒልክ ክፍተቱን በመጠቀም እንጦጦ ማሪያም ላይ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መሆናቸውን በይፋ አወጁ። ይህን ተከትሎ የትግራዩ ራስ መንገሻ ዮሀንስ ንግስናው ለእኔ ይገባል በሚል ሽፋን ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ አልገብርም በማለት አንገራገረ። ይህን ጊዜ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የወሎውን ራስ አሊ (የኋለኛው ንጉስ ሚካኤል) እና የሀረርጌውን ራስ መኮንን (የአጼ ኃይለስላሴ አባት) ወደ ትግራይ በመሄድ ህግ እንዲያስከብሩ ትዕዛዝ በመስጠቱ የሁለቱ ራሶች ጦር የራስ መንገሻን ጦር ድባቅ በመምታቱ ራስ መንገሻ ከዋሻ ውስጥ ተደብቆ ተገኘ። ከዛም በምርኮ መልክ ወደ መሀል አገር እንዲመጣና በአንኮበር በግዞት እንዲቀመጥ ተደረገ። በምትኩም በአጼ ዮሀንስ የተሳሳተና በስጋት ላይ በተመሰረተ ውሳኔ አማካኝነት ከስልጣን ተገልሎ የነበረውን ራስ አሉላ አባነጋን የትግራይ ገዥ አድርገው በመሾም የትግራይ ሕዝብ በራሱ ልጅ እንዲተዳደር አደረገ። ከትግራይ አንጻር ያለው ታሪካዊ እውነታ በአጭሩ ይኸ ሆኖ እያለ የአክራሪ ብሔርተኛ ልሂቃን አላዋቂ ሳሚ … እንደሚባለው የተሳሳተ ትርክት ላይ በመመስረት አጼ ምኒልክ በኤርትራና ኢትዮጵያ የሚገኙ ትግሬዎችን ለሁለት ከፍሎ አዳከመን ሲሉ ይሰማሉ። የትግራይ ልሂቃን አቻ የሆኑት የኦሮሞ ልሂቃንም ዳግማዊ አጼ ምኒልክ አርሲ ላይ በተካሄደ ውጊያ ጡት ስለቆረጠ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በየትኛውም የታሪክ መዝገብ ላይ ያልሰፈረ ትርክትን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ። በዚህም የተሳሳተ ትርክት ምክንያት ምንም የማያውቁ እንቦቀቅላ ህጻናትና ገና ምኑንም ያልዙት ታዳጊ ወጣቶች በአማራ ሕዝብ ላይ የጥላቻ ስሜት ይዘው እንዲያድጉ በመደረግ ላይ ነው። የሚገርመው ነገር እምየ ምኒልክ ተበታትኖና ለቅኝ ገዥዎች ወረራ ተጋልጦ የነበረውን የኦሮሞ ሕዝብ ወደ አንድ ማሰባሰብ በመቻላቸውና የጅማና የወለጋ አካባቢዎችን ደግሞ በራሳቸው ባላባቶች ማለትም በጅማ አባ ጅፋር እና በኩምሳ ሞረዳ እንዲመሩ ማድረጋቸው ለእነዚህ አክራሪ ብሔርተኛ ልሂቃን በመልካምነት ሊታያቸው አለመቻሉ ነው። ሁለተኛውን ምሳሌ በቀጣዩ ጽሁፌ እመለስበታለሁ። @ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

Source: Link to the Post

Leave a Reply