የአዉሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በአማራ ክልል የቀጠለዉ ግጭት ህብረቱን እንዳሳሰበዉ ገለጹ፡፡

የአዉሮፓ ህብረት በአማራ ክልል የቀጠለዉ የትጥቅ ግጭት እንዳሳሰበዉ የገለጹት ሃላፊዉ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የንጹሃን ዜጎች መሞት እና መጎዳት በእጅጉ ያሳስበዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶም በአገሪቱ ከፍተኛ እስር መኖሩን አንስተዋል፡፡

ህብረቱ፤የአፍሪካ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለንጹሃን ጥበቃ እንዲደረግ ፣ ግጭቶች እንዲቆሙ እና በሁለቱ ሃይሎች መካከል ንግግር እንዲደረግ የሚያደርጉትን ጥረት መቀላቀሉንም ነዉ ቦሬል ያስታወቁት፡፡

ህብረቱ በፖለቲካዊ ስምምነት ሰላም ለማምጣት የሚደረግ ንግግር፣ ስምምነት እንዲሁም ማንኛዉንም ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ነዉ የገለጹት፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለአገሪቱ የወደፊት ሰላም በጋራ እንዲሰሩ እጠይቃለሁ ያሉት ቦሬል፤ ለዚህም በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሚቀመጠዉ አሰራር መሰረት የንግግር እና የስምምነት መንገድን መከተል አለባቸዉ ነዉ ያሉት፡፡

እስከዳር ግርማ
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply