የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ህገ ወጥ ስደተኞችን ለመቀበል ከህብረቱ ጋር መተባበር ባለመቻሉ የቪዛ ገደብ እንዲጥል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/MEJLBr25xf3qP_GIq2aPY51yjaqs62oGaujNJABmT-y46_clgO3OOoCoi7aSh4-Cre0U_S0j5eg7hkdBJrw7I2gqCpHptdb6aBdqMgqPaXknKRvzT65voHzgoP9BA6UnxGf6dsCKyx4HR_y3SEjynU7knJFrQEUEXscKX8C5v8t7HHqSJeeC9OMXQD8MhSv3k2K0ihjDVPYDjIHkWXasM_l7kaaTgFWmAvEiqruAOhsnNCwcrffoRlIVjbEK9aD5DEZehd8csDbdt5qfuh9HxLH-x5AKUjM2BKjkcUkZqO4pRu4bChOfEZY4ItAVE3daXJJcmq66Erk6pgV13t6SJQ.jpg

የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት ህገ ወጥ ስደተኞችን ለመቀበል ከህብረቱ ጋር መተባበር ባለመቻሉ የቪዛ ገደብ እንዲጥል ምክንያት እንደሆነው የአውሮጳ ህብረት ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የህብረቱ እርምጃ የተሰማው በጦርነት ከተመሰቃቀሉ የአፍሪቃ ሃገራት በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት የሜድትራንያን ባህርን አቋርጠው የሚመጡትን ስደተኞች ለማስቆም ብርቱ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው።

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ህብረቱ አባል ሃገራት የገቡ እና መመለስ ያለባቸውን ዜጎቿን እንድትቀበል በትብብር ለመስራት ሲደረግ የነበረውን ግምገማ ማጠናቀቁን የገለጸው የአውሮፓ ህብረት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ትብብር «በቂ አይደለም » ብሏል።

የአውሮጳ ህግ አውጪዎች የተሻሻለውን የፍልሰት ስርዓት ባለፈው ወር መጨረሻ ነበር ያጸደቁት ።

የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ማእከል እንዳለው የፍልሰት ስርዓት ማሻሻያው ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ህብረቱ የሚገቡ የስደተኞችን ቁጥር ይቀንሳል።

የሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply