የአውሮፓ ህብረትና ብሪታንያ በይፋ ተለያዩ

የአውሮፓ ህብረትና ብሪታንያ በይፋ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቋ ብሪታንያ እና የአውሮፓ ህብረት በይፋ ተለያይተዋል፡፡

ሃሙስ ከእኩለ ሌሊት በኋላም ብሪታንያ የአውሮፓ ህብረትን ህግ መከተል ያቆመች ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም ሃገራቸው ነፃነቷን በእጇ ይዛለች ሲሉ ተደምጠዋል።

ብሪታንያውያን በፈረንጆቹ 2016 ከአውሮፓ ህብረት ለመነጠል በህዝበ ውሳኔ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ተደጋጋሚ ድርድሮችና ውይይቶች ተደርገው በመጨረሻም የብሪታንያ እና የአውሮፓ ህብረት ፍቺ ሌሊቱን ይፋ ሆኗል፡፡

በትናንትናው እለትም ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር የደረሰችው የንግድ ስምምነት ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉም የሚታወስ ነው፡፡

የንግድ ስምምነቱ ብሪታንያን ከአውሮፓ ህብረት የጋራ ገበያ የሚያስወጣ ሲሆን፥ በአንጻሩ በሃገሪቷ ሸቀጦች ላይ ቀረጥን ግን አይተገብርም፡፡

ከህብረቱ ጋር የተፈጸመው ፍቺ በቦሪስ ጆንሰን እና ደጋፊዎቻቸው ቢወደስም ተቃዋሚዎችንም አስተናግዷል፡፡

ከዚህ ውስጥ በታላቋ ብሪታንያ የሚጠቃለሉት ስኮትላንድ እና አየርላንድ የብሪታንያን ከህብረቱ መውጣት ተቃውመዋል፡፡

የስኮትላንድ ቀዳሚ ሚኒስትር ኒኮላ ስተርጂን ሃገራቸውን ዳግም ወደ ህብረቱ ለመቀላቀል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ስኮትላንድ በቅርቡ ወደ አውሮፓ ህብረት ትመለሳለችም ብለዋል በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የአውሮፓ ህብረትና ብሪታንያ በይፋ ተለያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply