የአውሮፓ ህብረት ለግብጽ 1ቢሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ፡፡

ግብጽ ኢኮኖሚዋን እንድትደግፍ ከአውሮፓ ህብረት አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር አግኝታለች፡፡

ሀገሪቷ ከዚህ በተጨማሪም ከህብረቱ እስከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር የምታገኝ ይሆናል ተብሏል፡፡

ህብረቱ ለግብጽ የሚሰጠውን ብድር ያጸደቀው ሃገሪቷ በጋዛ ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚዋ ክፍኛ መጎዳቱን ተከትሎ እንደሆነ ነው የህብረቱ ምግለጫ የሚጠቁመው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሃውቲ አማጺያን በቀይ ባህር አካባቢ እያደረሱት ያለውን ጥቃት ተከትሎ፣ ግብጽ ከዚህ አካባቢ ታገኝ የነበረው ገቢ በዕጥፍ መቀነሱን ተከትሎ ነው የብድር ስምምነቱ የጸደቀው ተብሏል፡፡

ግብጽ አለም አቀፍ ድንጋጌዎች እስካከበረች ድረስ ህብረቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀ ሲሆን በሃገሪቱ የሚታዩ የመብት ጥሰቶች መሻሻል ይገባቸዋል ሲልም ግልጻል፡፡

ግብጽ በቀጠናው እየተጫወተችው ያለው የአሸማጋኝነት ሚናዋ አጠናክራ እንድትቀጥል ያሳሰበው ህብረቱ ለአፍሪካ ብሎም ለመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋት የግብጽ ሚና የጎላ ነው ብሏል፡፡

የካይሮ መንግስት በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 አመት ከአለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች እና ከሃገራት ያገኝችው የብድር መጠን 13 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነም ነው የአፍሪካ ኒውስ መረጃ የሚያሳየው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 07 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply