የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በምስራቅ ሜዲትራንያን ዘላቂ የሆነ የፀረ ሽብርተኝነት ስራ ለመስራት መስማማታቸው ተገለፀ፡፡

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬልና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንክን በብራስልስ ባደረጉት ቆይታ በምስራቅ ሜዲትራንያን የፀረ ሽብርተኝነት ስራን ጨምሮ በሰፊው የውጭ ግንኙነት ፖሊስ እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጻል፡፡

ሁለቱ ዲፕሎማቶች ከሽብርተኝነት እና ደህንነት በተጨማሪ ሩሲያ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር ያላትን የግጭት ባህሪ ለመፍታት እና ሩሲያ እንደዚህ አይነት የአካሄድ መንገዶችን እንድታቆም ለማበረታታት በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል፡፡

ዲፕሎማቶቹ አክለውም በምስራቅ ሜዲትራንያን የሽብር ቀጠናዎች ላይ ከቱርክ ጋር በትብብር በመስራት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ወጥነዋል፡፡ለዚህም ይረዳን ዘንድ ከቱርክ ጋራ የሚያደርጉትን ስምምነት አፅንዖት ሰጥተው ተወያይተውበታል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡

ቀን 17/07/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply