የአውሮፓ ህብረት ከሰላም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ መተግበር በኋላ 1 ቢሊዮን ዩሮ እርዳታ ለኢትዮጵያ እሰጣለሁ አለ::

ከሰላም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ መተግበር በኋላ አንድ ቢሊዮን ዩሮ እርዳታ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል።

ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የልማት ትብብር እና የሚሰጠውን የኢኮኖሚ ድጋፍ ለመቀጠል የሰላም ስምምቱ በዘላቂነት ተግባራዊ መሆን እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ወደ 90 ሚሊዮን ዩሮ ከሚጠጋው የበጀት ድጋፍ በተጨማሪ፣ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ያዘጋጀውን አንድ ቢሊዮን ዩሮ የልማት እርዳት በጦርነቱ ምክንያት ሳይጸድቅ ቀርቶ ነበር፡፡

ህብረቱ የበጀትና ኢኮኖሚያዊ ድጋፉን ለማስቀጠል የፕሪቶሪያውን በቋሚነት ግጭትን የማቆም ስምምነት ተፈጻሚነትን እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል፡፡

ህብረቱ በአውሮፓ ካውንስል በኩል ባወጣው መግለጫ፤ በተኩስ አቁም፣ ያልተገደበ የእርዳታ አቅርቦት፣ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ረገድ ተጨባጭ መሻሻል መኖሩ የህብረቱን የልማት ትብብር እና የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማስጀመር እንደሚያስችል አስታውቋል።

ይህ አይነቱ የሰላም ስምምነቱን ተፈጻሚነት ብድርና እርዳታ ለመስጠት እንደ ቅድመ ሁኔታ መጠቀም በሌሎች አገራትና አለም አቀፍ ተቋሞችም እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply