የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ጋር ተያይዞ  በቡና ምርት ላይ ሊጥል ያሰበውን ዕገዳ ለማስቀረት ኢትዮጵያ አጭር ጊዜ ነው ያላት ተባለ።የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆኑ ምርቶች ብቻ…

የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ጋር ተያይዞ  በቡና ምርት ላይ ሊጥል ያሰበውን ዕገዳ ለማስቀረት ኢትዮጵያ አጭር ጊዜ ነው ያላት ተባለ።

የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆኑ ምርቶች ብቻ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት እንዲገቡ የሚፈቅደ የ EUDR ደምብ በቡናው ዘርፍ ትልቅ ስጋት  እንደፈጠረ መገለፁ ይታወሳል።

የቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ግዛት ወርቁ  ያለን ጊዜ አጭር ነው  ሁሉም አካል የድርሻውን ማድረግ ካልቻለ ከቡና ዘርፍ የሚገኘው ምንዛሬ ችግር ውስጥ ይወድቃል ነው ያሉት።

መረጃዎችን መዝግቦ የማስረዳትና የማቅረብ ችግር ስላለብን እንጂ   ኢትዮጵያ ውስጥ በጫካ ምንጠራ የሚመረት  የቡና ተከላ እና  ምርት ብዙም የለም ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት በ 2025 ተግባራዊ ሊያደይርገው ያቀደው የፀረ ደን ጭፍጨፋ ደንብ በቡናው ላይ ትልቅ ጫና እንደሚያሳድርም ተናግረዋል።

መረጃዎችን መዝግቦ ይዞ በጫካ ምንጠራ የተመረተ ቡና እንደሌለ በሳታላይት አንስቶ ማስረጃ በማቅረብ የሚሉት ቡና በምንጠራ እንዳልመጣ በማሳየት ችግሩን መቅረፍ  እንደሚቻል ተናግረዋል።

በወጣው ህግ መሰረት በአውሮፓ ህብረት ገበያ ላይ መቅረብ የሚችሉት ምርቶች ህጋዊ የሆኑ፣ ከደን መጨፍጨፍና መራቆት ጋር ያልተገናኙ ምርቶች ብቻ መሆን እንዳለባቸው መገለፁ የሚታወስ ነው።

ከአውሮፓ ህብረት 27 አባል ሀገራት 20 ያህሉ የፀረ-ደን መጨፍጨፍ ህጉ እንዲዘገይና አነስተኛ የደን መጨፍጨፍ አደጋ አለባቸው ተብለው በሚታሰቡ አገሮች የሚገኙ አምራቾችን ታሳቢ በማድረግ ከህጉ ነፃ እንዲያደረጉ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ህብረቱን መጠየቃቸው ይታወሳል።

ለአለም አሰፋ 

ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply