የአውሮፓ ቻምበር በኢትዮጵያ የግብር አስተዳደርን በማሻሻል ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ ይፋ አደረገ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ቻምበር በኢትዮጵያ የግብር አስተዳደርን በማሻሻል ላይ ያተኮ…

የአውሮፓ ቻምበር በኢትዮጵያ የግብር አስተዳደርን በማሻሻል ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ ይፋ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ቻምበር በኢትዮጵያ የግብር አስተዳደርን በማሻሻል ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ በዛሬዉ ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

የአውሮፓ ቻንበር ኤክስኪዩቲቪ ዳይሬክተር አቶ ባሃሩ ተመስገን ፤የሰነዱ ዓላማ በኢትዮጵያ ከግብር አስተዳደር ጋር በተያያዘ የግሉ ዘርፍ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በመለየት ምቹ ሁኔታ መፍጠርና የውጭ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ መሳብ ነው ብለዋል።

የግብር አዲተሮች ያልተገደበ ሥልጣን፣ ስለተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ዓለም አቀፍ የግብር ስምምነቶች የእውቀት ውስንነት ፣ ወቅታዊ የግብር መረጃ በጊዜው አላማሳወቅ እንደችግር ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም የታከስ አዲትን ጥራት የሚቆጣጠረው ተቋም ማንነት ግልጽ አለመሆን እንደችግር ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ናቸው።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ በበኩላቸዉ የፖሊሲ ሰነዱ ፍትሀዊና የተሻለ ግልጽነት ያለው የግብር አስተዳደር ሂደት እንዲኖር ያደረጋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ የአውሮፓው ኢንቨስትመንት የንግድ ማህበር በአሁኑ ጊዜ 180 አባላት ያሉት ገለልተኛ ማህበር ነው ብለዋል።

የሮቻም ኢትዮጵያ አሳታፊ በሆነ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ እጅግ ተፈላጊ ከሆኑት የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች እንዷ እንድትሆን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ሰምተናል።

በመጨረሻም የአውሮፓ የንግድ ሥራዎችን የመረጃ ልውውጥን በማጎልበት፣ የትብብር መድረኮችን በማቋቋምና የንግድ ሁኔታን በጋራ ለማሻሻል ከመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት በማድረግ የመደገፍ ስራ ይሰራል ተብሏል።

በልዑል ወልዴ

ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply