የአውሮፓ ፓርላማ የኢራን አብዮታዊ ዘብን በሽብርተኝነት መፈረጁን ቴህራን አወገዘች

https://gdb.voanews.com/df62603e-839e-4d4a-b371-b2d9d806ef58_w800_h450.jpg

የአውሮፓ ፓርላማ የኢራን አብዮታዊ ዘብን በአሸባሪ ቡድንነት በመፈረጅ ድምፅ የሰጠ ሲሆን ኢራን ዕርምጃውን አውግዛለች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር-አብዶላሂያን ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ጋር በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን የአውሮፓ ፓርላማ የወሰደውን ዕርምጃ አጥብቀው ማውገዛቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው አስታውቋል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ጥቃት ማድረሱንና ዩክሬን ለሚገኙ የሩሲያ ኃይሎች ድሮኖች መስጠታቸውን በማውገዝ የአውሮፓ ፓርላማ አሳሪ ያልሆነ ውሳኔውን ያስተላለፈው ትናንት ረቡዕ ነበር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply