የአየር ንብረት ለዉጥ ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ለመተግበር የሚያስችል 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ መገኘቱን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለ…

የአየር ንብረት ለዉጥ ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ለመተግበር የሚያስችል 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ መገኘቱን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለአራት ቀናት የሚቆይ በተለይም አየር ንብረት ለዉጥ ላይ መሰረት ያደረገ ዎርክሾፕ በዛሬዉ ዕለት አስጀምሯል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከ ‘Global environment facility (GEF)’ ወይንም ከዓለም የአካባቢ ፋሲሊቲ በተገኘ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበሩ እና ሊተገበሩ እየተዘጋጁ ያሉ ከ20 በላይ የአየር ንብረት ለዉጥ፣የኬሚካል አደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም የብዝሀ ህይወት ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚሠራበት አስታውቋል።

በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የዓለም የአካባቢ ፋሲሊቲ ተወካይ እንዲሁም የዓለም አቀፍ አካባቢ ስምምነቶች ድርጅት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ መንሱር ደሴ ፣በዓለም አቀፍ ያሉ የአየር ንብረት ለዉጥ፣የብዝሀ ህይወት እንዲሁም የአካባቢ ብክለትን በተመለከተ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት መፈራረማቸዉን ገልፀዋል።

ከስምምነቱ በኋላ በትግበራ ላይ የሚገኘዉ ይህ ስምምነት፣ የአደጉ ሀገራት በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ገንዘብ፣ ቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

ገንዘቡ በተለያዩ መንገዶች ከአደጉ ሀገራት ወደ ታዳጊ ሀገራት እንደሚላክ የገለፁት አቶ መንሱር፣ ለኢትዮጵያ የተደረገዉ የአሁኑ ድጋፍ ወደ አለም አቀፉ የገንዘብ ቋት በሆነዉ የአለም አካባቢ ፋሲሊቲ አማካኝነት መሆኑን ገልፀዋል።

ከዛሬ መስከረም 21 እስከ 26/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄደዉ ወርክሾፕ ከ18 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 150 ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉበት ተገልፃል።

በአቤል ደጀኔ

መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply