#የአይን ጠብታ አጠቃቀም ከስሜት ህዋሳት መካከል አንዱ የሆነው አይናችን የብርሀን መኖርን የሚያሳውቀንና ነገሮችን እንድናይ የሚያስችለን በጣም አስፈላጊው አካላችን ነው፡፡ብዙ ሰዎች አይና…

#የአይን ጠብታ አጠቃቀም

ከስሜት ህዋሳት መካከል አንዱ የሆነው አይናችን የብርሀን መኖርን የሚያሳውቀንና ነገሮችን እንድናይ የሚያስችለን በጣም አስፈላጊው አካላችን ነው፡፡
ብዙ ሰዎች አይናቸው ሲደርቅ፣ አለርጂ ወይም የአይን መቅላት እና አይናቸው ላይ ሌሎች ችግሮች ሲያጋትሙት ለዛ ነገር ማስታገሻ የአይን ጠብታዎችን ይጠቀማሉ፡፡

ታድያ የአይን ጠብታዎችን በምነጠቀምበት ግዜ መደረግ የሚገቡዋቸው ነገሮች ምንድናቸው የሚለውን ማብራሪያ እንዲሰጡን የአይን ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ጉተታ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

#የአይን ጠብታ #ምንድነው?

የአይን ጠብታ እንደማንኛውም መድሃኒት በጠብታ መልክ የተዘጋጀ መድሃኒት መሆኑን ባለሙያው ይናገራሉ፡፡
ስለዚህ የአይን ጠብታ ዝምብሎ ያለ ምክንያት የሚወሰድ አለመሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ባለሙያው ያለሃኪም ትእዛዝ ቢወሰድ ብዙም ችግር የሌለው ለአይን ድርቀት የምንጠቀምባቸው የአይን ማለስለሻ የአይን ጠብታዎች ብቻ መሆናቸውን
ተናግረዋል፡፡

ከእንባ ማለስለሻ ውጪ ያሉ የአይን ጠብታዎች ግን በጣም በጥንቃቄ እና ከሀኪም ትእዛዝ ውጪ መወሰድ እንደሌለባ ቸው ያስጠነቅቃሉ፡፡
ያለሃኪም ትእዛዝ የምወስዳቸው

#የአይን ጠብታዎች ምን #ሊያስከትሉ ይችላሉ?

– በሽታውን ማባባሰ
– የአይን ግፊት መጨመር
– አላስፈላጊ የሆነ ድርቀት
– አለርጂ ሊያስከትሉብን እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

#የአይን ጠብታዎችን ስንወስድ ምን አይነት #ጥንቃቄ መወሰድ አለበት ?

– አንድ ጠብታ በቂ ነው ሁለት ሶስት ጠብታ ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡
– አይናችን ውስጥ መግባቱን እርግጠኛ መሆን አለብን ፡፡
– ጠብታውን ካደረግን በኋላ አይናችንን መጭመቅ ሳይሆን እንደሚተኛ ሰው መክደን ፡፡
– ጠብታውን ከማድረጋችን በፊት የእጅ ንፅህናን መጠበቅ ፡፡
– በታዘዘልን ሰአት መሰረት መጠቀም ፡፡
– ከተጠቀምን በኋላ በትክክል ከድነን ልጆች የማይደርሱበት ማስቀመጥ እንደሚገባ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም መድኃኒት ብለን የምናስባቸወ ነገሮች የሚዋጡ ናቸው፡፡ ነገር ግን የአይን ጠብታም ቢሆን መድሀኒት ስለሆነ የተሰራለት እና የታቀደለት ነገር አለው፡፡ ሰለዚህ ስላገኘን ብቻ መጠቀም ተገቢ አለመሆኑን እና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የተለያዮ የአይን ጠብታዎችን ከተጠቀምን በኋላ አለርጂ ወይም የአይን መቆጣት ምልክት ካለ ጠብታውን አቁሞ ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ጉተታ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው
መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply