
የአዲስ ቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ሳህለገብርኤል ይትባረክ በጠዋት የዜና ማንበብ ክፍለጊዜ ሰአቱን ጠብቆ ጥቁር በመልበስ ዜና ማንበብ ቢጀምርም ከስቱዲዮ አቋርጠው እንዲወጣ አድርገውታል ተብሏል:: በዚህ የዜና ሰአት ፋንታም ሌሎች ፕሮግራሞች ተለቀውበታል:: በተመሳሳይ የጣቢያው ጋዜጠኞች እና የአገልግሎት ዘርፍ ሰራተኞችም ጥቁር በመልበሳቸው ምክንያት ከግቢ እንዳይገቡ ታግደዋል:: በትናንትናው እለትም ተመሳሳይ ችግር ተፈጥሮ ሰራተኞች ተመልሰው እንደነበር በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች መዘገቡ አይዘነጋም::
Source: Link to the Post