You are currently viewing የአዲስ አበባ ህዝብ ገንዘብ እያዋጣ የወለጋ ተፈናቃዮችን መመገብ ጀመረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ ከወለጋ አዲስ አበባ ከገቡ…

የአዲስ አበባ ህዝብ ገንዘብ እያዋጣ የወለጋ ተፈናቃዮችን መመገብ ጀመረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከወለጋ አዲስ አበባ ከገቡ…

የአዲስ አበባ ህዝብ ገንዘብ እያዋጣ የወለጋ ተፈናቃዮችን መመገብ ጀመረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከወለጋ አዲስ አበባ ከገቡ ቦኃላ “የሀገር ገፅታ ታበላሻላችሁ” ተብለው ወደ አርሲ ተወስደው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። የካቲት 7 ቀን 2014 አዲስ አበባ እንደገቡ የተናገሩት ተፈናቃዮች፣ የሚያርፉበት ቦታ አጥተው እየተንከራተቱ ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ ለመጀመሪያ ግዜ አዲስ አበባ ሲገቡ፣ በመስቀል አደባባይ ካረፉ በኋላ በዚያው አቅራቢያ በሚገኘው ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው ሰንብተዋል። ከዚያም የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ ሲጀመር “ለመንግሥት ገፅታ ጥሩ አይደለም” በሚል ወደ አሩሲ ተወስደው መቆየታቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል። ተፈናቃዮቹ በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ መንገድ ላይ ተሰብስበው የቆዩ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ ጃንሜዳ አካባቢ ተሰብስበዋል። እንቅስቃሴያቸውን ሁሉ ፖሊስ በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮልም በቦታው በመገኘት ተፈናቃዮችን አነጋግረዋል። ጋዜጠኞች በቦታው ቢገኙም፣ እንዳይቀርፁና ጉዳዩን እንዳይዘግቡ ተከልክለዋል። የባልደራስ አመራሮች ግን፣ “ብትፈልጉ ልታስሩን ትችላላችሁ” በማለት ያለ ፖሊስ ፍቃድ ቀረፃ አድርገዋል፣ ተፈናቃዮቹንም አነጋግረዋል። አመራሮቹ ወደ ቦታው ከመድረሳቸው በፊት፣ የባልደራስ አባል የሆነው ሰለሞን አለምኔ፣ “ተፈናቃዮቹን ፎቶግራፍ አንስተሃል” ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ሲሆን፣ የባልደራስ አመራሮች ተከራክረው አስለቅቀውታል። የባልደራስ አመራሮች በቆይታቸው ያነጋገሯቸው ተፈናቃዮች፣ ጅምላ ጭፍጨፋውን እና ማፈናቀሉን እየፈፀሙ ያሉት የክልሉ ባለሥልጣናት ከኦነግ/ሸኔ ጋር በመመሳጠር መሆኑን ተናግረዋል። ሕፃናት፣ አረጋውያን እና ነፍሰ ጡሮች በሆሮጉድሩ ወለጋ በካራ መታረዳቸውንም ገልፀዋል። ተፈናቃዮቹ ምግብ፣ ልብስና መጠለያ እንደሌላቸው በመጥቀስ የአዲስ አበባ ኗሪ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሎም ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል። የባልደራስ አመራሮች ወደ ቦታው ሲደርሱ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ ገንዘብ አዋጥቶ ተፈናቃዮቹን ምግብ እያበላ ነበር። ለዚህ በጎ ድርጊቱ ተፈናቃዮቹ የአዲስ አበባን ህዝብ አመስግነዋል። የባልደራስ አመራሮችም በሰጡት አስተያየት፣ “በአዲስ አበባ ህዝብ በጣም ኮርተናል፣ በዚሁ ሊቀጥል ይገባል። መንግሥት ለተፈናቃዮቹ ማረፊያ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል” ብለዋል ሲል የዘገበው የባልደራስ ሚዲያ ክፍል ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply