የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ወደ 8ሺህ 5መቶ የሚጠጉ እንስሳትን ለእርድ ማዘጋጀቱ ተገለፀ።የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ7ሺህ5መቶ እስከ 8ሺህ 5መቶ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/k9Ed4SNmqZ4m5zYiok0i7VvSt9eNhs_AP0FTUYk2eFxEUHV6tAcFKs8lf6f_BoY5Det-5C5RbstvBmxgtH0TdeeKGtYHpqaDESRLel3K7TdM9Ido_0dE9mYWU3-89DFtAvNJh1uI8Lti1hogSImMqAlpriQl41o0MpPnJTF-k7_xE3pLur1Ox9ibZge7wbQ38gBzwXaSNrct4S7QcjLdL8DInZHF9PBMa0LsyrS2t2MvnnMbX3zAH-12YEFpPmm8fufgxm6QwwFVTIMT5J9uYxHKpCmh34JKs05UEd0M4kPuKL9BPsmbmD7ZrRBnfbRR5cUaqcpSIt67Ukn9ykIDLQ.jpg

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ወደ 8ሺህ 5መቶ የሚጠጉ እንስሳትን ለእርድ ማዘጋጀቱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ7ሺህ5መቶ እስከ 8ሺህ 5መቶ የሚጠጉ እንስሳትን ለእርድ አዘጋጅቻለሁ አለ።

ከ4 ሺህ እስከ 4ሺህ 5መቶ ትላልቅ እንስሳቶችን እንዲሁም ከ3 እስከ 4ሺህ ደግሞ በግ እና ፍየል ማዘጋጀቱን የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እድሪስ ተናግረዋል።

ከእርድ በኋላ አንድ ኪሎ የበሬ ስጋ በ5መቶ70 ብር፣ ሙሉ ፍየል በ5መቶ10 ብር እንዲሁም ሙሉ በግ ደግሞ በ5መቶ ብር እንደሚሸጥ ነው የገለፁት።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከሙሉ በግና ፍየል ውጪ የ10 እና የ15 ብር ጭማሪ ኖሮት በግማሽ የሚሸጥ እንዳለም ነው የተናገሩት።

ከመደበኛ ዕርድ በተለየ መልኩ በዚህ የበዓል ወቅት 2 መቶ ጊዜያዊ የዕርድ ሰራተኞችን እንዲሁም 50 የተረፈ ምርት አስወጋጅ ባለሙያዎችን መቅጠሩንም አቶ ሰይድ ተናግረዋል።

የአቃቂ ቅርንጫፍን ጨምሮ 37 ተሽከርካሪዎችም ዝግጁ ሆነው እየጠበቁ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በእስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply