You are currently viewing የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን ምዝገባ ሊያካሂድ ነው

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን ምዝገባ ሊያካሂድ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን ምዝገባ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በምዝገባው ተጠቃሚ የሚሆኑት በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት መርሐ ግብር ተመዝግበው ቤት ለማግኘት የሚጠባበቁት ናቸው ተብሏል።
ምዝገባውን በኦንላይን እንደሚከናወን ቢሮው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በማህበር የተደራጁ የመርሐ ግብሩ ተጠቃሚዎች እጣ ከወጣላቸውየቤት ግንባታ ወጪውን 70 በመቶ በባንክ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
30 በመቶ ሴት ተመዝጋቢዎች እንዲሁም 20 በመቶ የመንግስት ሰራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ተብሏል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ በመርሐ ግብሩ በ2005 ዓ.ም ተመዝግበው ቁጠባ ያቋረጡ በማህበር ቤት ልማቱ ሊመዘገቡ አይችሉም ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን ምዝገባ ሊያካሂድ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply