የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ አደረገ

ዕረቡ ሐምሌ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ጀመሮ ተግባራዊ የሚደረግ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር የሚደርስ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ለውጥን ብቻ መሰረት በማድረግ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ማስተካከያ ማድረጉን ነው ቢሮው የገለፀው።

የሸገር እና አንበሳ ከተማ አውቶብስ ታሪፍ በዚህ ወር መጨረሻ ማስተከከያ እንደሚደረግም ተነግሯል።

ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ዝርዝር ከሥር ተያይዟል።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply