የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ 2መቶ 74 የንግድ ሱቆችን አሽጊያለሁ አለ።

የአዲስ አበባ ንግድ ብሮ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰውነት አየለ 2መቶ 74 የንግድ ሱቆች ታሽገዋል ብለዋል፡፡

የንግድ ሱቆቹ የታሸጉት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የንግድ ፍቃዳቸውን ከሃምሌ አንድ እስከ ታህሳስ 30 ባሉት ጊዜያት ውስጥ እደሳ ባለማድረጋቸው ነው።

አቶ ሰውነት 3 መቶ 84 ሺህ 4 መቶ 19 ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳቸውን ለማደስ ቢሮው በያዘው እቅድ መሠረት 3 መቶ 6 ሺህ 4 መቶ 80 ያህሉ ነጋዴዎች ፍቃዳቸውን አድሰዋል ብለዋል።

ከ50 ሺህ በላይ የንግድ ፍቃድ ከፍተዉ ባላሳደሱ የንግድ ተቋማት ላይ የበር ለበር ክትትል እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል ።

እስካሁን በተደረገውም የበር ለበር ክትትል በ 2 መቶ 74 ሳያሳድሱ በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውንም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል ።

በልዑል ወልዴ
ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply