የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በሰጡት መግለጫ ጃንሜዳ የሚገኘው ጊዜያዊ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ የገበያ ስፍራ የከተማው አስተዳደር ባዘጋጀው የገበያ ማዕከል እንዲዘዋወሩ በተወሰነው መሰረት የዕጣ ማውጣት ስርዓቱ ተጠናቆ ውል መዋዋል ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ ጃንሜዳ የነበረው አትክልት ተራ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በተገነባው የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ገበያ ማዕከል ተዘዋውሮ ስራ የሚጀምር መሆኑን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

The post የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply