የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በግንባታ ላይ  ባሉ የመንገድ ቱቦዎች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት እና ለሚለቀቁ ፍሳሾች ርምጃ እንሚወስድ አስታወቀ፡፡

በግንባታ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ የሚቀርብበት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ በተለያዬ ቦታዎች እየተገነቡ ባሉ መንገዶች ፍሳሾችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቋል፡፡

በከተማዋ የነባርና አዳዲስ ድልድዮችን ጨምሮ የከተማውን የትራፊክ ፍሰትና የህብረተሰቡን የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ያፋጥኑ ዘንድ በርካታ የህዝብ ገንዘብ ወጥቶባቸው መንገዶች ይሰራሉ ነገር ግን በአዲስ በሚሰሩ መንገዶች ላይ አስተማማኝ የውሃ መውረጃ ቱቦዎች ስለማይሰሩላቸው ከመኖሪያ ቤቶችና ከፋብሪካ በሚወጡ ፈሳሾች መበከላቸው ይነገራል፡፡

አዲስ በመገንባት ላይ በሚገኘው እና ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት የአቃቂ ዱከም መንገድ አንዱ ነው፡፡ መንገዱ ከሚደረግለት ግንባታ ጎን ለጎን የሚፈሰው ቆሻሻ በእንቅስቃሲያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በበኩሉ ድርጊቱ ስር የሰደደ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመንገድ ግንባው ወቅት ከሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች መካከል ዋነኛው በውሃ መውረጃዎች ላይ የሚለቀቅ ፈሻስና ደረቅ ቆሻሻዎች መሆናቸውን የባለስልጣኑ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ እያሹ ሰሎሞን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

***************************************************************************

ቀን 04/05/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

ምስል፡- የተበላሹ መንገዶች

Source: Link to the Post

Leave a Reply