የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ እንደገለጹት፤ የተጠያቂነት አሠራር እንዲሰፍን እየተሠራ ይገኛል። የሕዝቡን መሰረታዊ ችግር ከመፍታት አንጻር የተቃኘ የክትትልና ግብረ መልስ አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል። በተገኙ ግኝቶች መሰረት አፋጣኝ የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ መደረጉንም አመልክተዋል።

ምክር ቤቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች መሠራታቸውን የገለጹት አፈ ጉባኤዋ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ላይ ሰፊ ተሳትፎ መደረጉን ተናግረዋል።

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ዋንጫ ላይ ከተማ አስተዳደሩ ያደረገው እንቅስቃሴ ምስጋና የሚቸረው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ሂደት ለመከላከያ ሠራዊቱ ያለውን ድጋፍ በተግባር ማሳየቱንም ተናግረዋል።

የሕገ መንግስት አስተምህሮ ላይ መሠራቱን የገለጹት አፈ ጉባኤዋ፤ የክልሎችን አንድነት ለማጠናከር የሕብረ ብሔራዊ ችቦ በከተማዋ እንዲዘዋወር መደረጉንም አስታውሰዋል።

የብሔር ብሔረሰቦች ኤግዚቢሽን እንዲዘጋጅ ተደርጎ በርካታ ታዳሚዎች እንዲገኙ መደረጉንም ገልጸዋል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል።

የከተማው ምክር ቤት የራሱን ህንጻ ለመገንባት የሚያስችለው ቦታ እንዲያገኝ በመደረጉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ አጋማሽ የአስተዳደሩ እና የፍርድ ቤቶች አፈጻጸም ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ እና የተለያዩ ሹመቶችን ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.

Source: Link to the Post

Leave a Reply