የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነዳጅ የጫኑ 8 የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታወቀ፡፡ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/uJk24y8XD1nKXplaSH8wnRG6mjKI17ANSUDL8P2-WifOHNJkv52Bry1kUPna3iV2E7SJ4RRCqeyYUMdjafp1_-9qgodPw4VIwTwxk2QmcgOH7M1JuTX542CbTQrlTec8OmAZvZffOUqT9hpDQM0E3r2TFzmi6EEYN5uRkJKleyDcbBmdxU3oZWZNpabjwSZZwT7d093KnahXhn-crTl87K3_2dqW9_cGqMHvEGh2Y_T-tGjWpwCALGG2Fi5wDRl5QgpzWY3TMMGjE087UZFMUnfnIYL-TA4Y1589hKSoRWNCyYwjgIVMPa2DwRwCtWiGaR-x6Myzz5wsm5mN-izfyg.jpg

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነዳጅ የጫኑ 8 የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታወቀ፡፡

ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ ስምንት የነዳጅ ካምፓኒዎች ቦቴዎች በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ ተወርሰዋል ተብሏል፡፡

የተወረሰው ነዳጅም በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ÷ ሕግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከቢሮው የተገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply