የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮች ለሞባይል ስልክ መግዣ እስከ 140 ሺህ ብር ድረስ ፈቀደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በጥር ወር ላይ በወሰነዉ ዉሳኔ መሰረት፣ ለከተማዋ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/mxq1NiXzQvhKumoHRu2Ypd3eANOX1H90s9_FOAE7YuyCISteMBHOsfuEVtlPURw8-fCbnumbPz9S6OgZQvSsCWoB_YHKLdwtfGgV5TERRL9ZKhojlt9VKV9bBxI4VSu8NVAi-CkekcpxY1h25Uhw8ja2VcDiLm2p8wj8sZxfnX2NXdLTry3ZMh22vuHrA906Fx3QQ5giFYPOFwJEd3lLE-7gZEQq8sV3P4PKKupvPTkKRfEJg1YQO3YqPiGcbziHjFWCTuqHBFVYujhuDCcaCKJKE7D7SThj0xB6kv6ziTyJL9g-MK69wH92VXy_2PHU2LqE-rf8i77i5Rsv_gVknA.jpg

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮች ለሞባይል ስልክ መግዣ እስከ 140 ሺህ ብር ድረስ ፈቀደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በጥር ወር ላይ በወሰነዉ ዉሳኔ መሰረት፣ ለከተማዋ አመራሮች የሞባይል ስልክ ቀፎ ግዢ መፍቀዱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል።
በዚህም መሰረት ለከንቲባ እና ለከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ 140 ሺህ ብር ተመድቧል።

ለምክትል ከንቲባ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ደረጃ ለተሿሙ አመራሮች እና ለምክትል አፈ-ጉባኤ ስልክ መግዣ 120 ሺህ ብር መወሰኑንም ሰምተናል።
ለክፍለ ከተማ 50 ሺህ ፣ለወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ የ40 ሺህ እንዲሁም ለወረዳ ቀሪ አመራሮች 30 ሺህ ብር የሚያወጣ የሞባይል ስልክ እንዲገዛላቸዉ ተፈቅዷል።
ይህንን የሚያስፈፅም ደብዳቤም በየክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች ጭምር መበተኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ተመልክቷል።

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply