የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ቆሻሻን ያለአግባብ የሚጥሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡የአፍሪካ መዲና እና በርካታ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ቆሻሻን ያለአግባብ የሚጥሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ መዲና እና በርካታ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የሚገኙባት ከተማዋ በሚገባት የንፅህና ደረጃ ላይ አይደተችም ተብሏል፡፡

በርካታ የህብረተሰብ ክፍል በፅዳት ንቅናቄ ስራዎች አካባቢዉን እያፀዳ የሚገኝ ቢሆንም፣አንዳንድ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በቸልተኝነት መዲናዋን እየበከሉ ይገኛሉ ሲሉ የከተማዋ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ሃላፊ ዶክተር እሸቱ ለማ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የከተማዋ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ያስተባበረዉ እና ለሶስት ወራት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ አካባቢ በካይ የሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን የመለየት እንዲሁም የመቅጣት እርምጃዎችን የሚይዝ ንቅናቄ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን አስታዉቀዋል፡፡

በዚህ ንቅናቄ ተቋማት በተናበበ መልኩ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና እርምጃ የመዉሰድ ተግባር ይከናወናል ተብሏል::

የመዲናዋ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ከደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር እንመራዋለዉ ያለዉ ይህ ንቅናቄ, የደንብ ማስከበር፧ የንግድ ቢሮ የትራፊክ ማኔጅመንት ፧ የመንገድ ባለስልጣን፧ የዉሐ እና ፍሳሽ፣ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በግብረ-ሐይሉ መካተታቸዉም ታዉቋል፡፡

ከቀላል እስከ ከባድ የገንዘብ እና ሌሎች አይነት ቅጣቶችንም የሚደነግገዉን ህግ ተፈፃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ ያለዉ ግብረ ሐይሉ፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የሙከራ ትግበራ ሲያከናውን መቆየቱን ተናግሯል፡፡

ግብረ-ሐይሉ ከነገ ታሕሳስ 012015 ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት እንደሚሰሩ ያስታወቀ ሲሆን፣ ግለሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸዉ 5 ሜትር ዙሪያ እና ድርጅቶች 10 ሜትር ራዲየስ እንዲያፀዱም አሳስቧል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply